Wednesday, August 19, 2015

አዳፍኔ ፍርሃትና መክሸፍ በእኔ ዕይታ!

በአብርሃም በዕውቀት
እርግጥ ነው ፕሮፌሰርን ለመተቼት የሚመጥን ቀርቶ ሊመጥን የሚጠጋ የዕውቀት ልክ ላይኖረኝ ይችላል፡፡ ለዚያውም ከፕሮፌሰርነታቸውም በላይ ሕይወት ያስተማራቸውንና በተቃውሞ ፖለቲካው ጫፍ የወጣ ዕውቅና ያላቸውን ፕሮፌሰር ጽሑፍ መንቀፍ በፌስቡክ ዳኞች በስቅላት ሁሉ ሊያስቀጣ ይችላል፡፡ ኧረ ራሳቸውም ሊሰቅሉኝ ባይችሉም ሊያሳቅሉኝ ይችላሉ፡፡ በእርግጠኝነት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምን ለመተቼት መሞከር የሚያስከትለውን ዘለፋና
ሌሎቹ የአገራችን ፊደላውያን ቀደም ሲል እንደገለፅኩት ጥቂት ‹‹ጆርናሎችን›› በተለያዩ ርዕሶች ላይ ከመጻፋቸው ውጭ ለዚያውም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውጭ አንባቢም ተጠቃሚም በሌላቸው ጭብጦች ላይ በአማርኛ ቋንቋ አንዳች ነገር ሲፅፉ አይታዩም፡፡ ለዚህም ነው ምሁራን ከማለት ተቆጥቤ ፊደላውያን የምላቸው፡፡ የፊደል እንጅ የተግባር ዕውቀት ስለሌላቸው፡፡
ነቀፌታ በሚገባ አውቀዋለሁ፡፡ ምክንያቱም እርሳቸው ከአገራችን ፊደላውያን መካከል ቁንጮ ናቸውና፡፡ ነገር ግን ፈርቶ ከመሞት ተናግሮ መሞት ይሻላል ብዬ ትችቴን ልቀጥል መሰለኝ? በቃ እንዲያውም ቀጠልኩ፡፡
ፕሮፌሰሩ ባለፈው ግንቦት ወር አዳፍኔ ፍርሃትና መክሸፍ የሚል መጽሐፍ ለገበያ አብቅተዋል፡፡ በነገራችን ላይ ፕሮፌሰር መስፍን በፈረንጅ ቋንቋ ሶስት አራት ‹‹ጆርናል›› ጽፈው የሚኮፈሱ ምሁራንን የሚያስከነዱ ቁጥራቸው በርከት ያሉ መጻሕፍትን ለኢትዮጵያውያን በራሳቸው ቋንቋ የሚጽፉ ሰው ናቸው፡፡ በዚህ ሥራቸው በእጅጉ አመሰግናቸዋለሁ፤ አደንቃቸዋለሁ፡፡
ወደ ተነሳሁበት የፕሮፌሰር መስፍን መጽሐፍ አዳፍኔ ፍርሃትና መክሸፍ ልመለስ፡፡ መጽሐፉ ዋነኛ ትኩረቱ ከዚህ በፊት ‹‹መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ›› በሚል ያሳተሙትንና በብዙዎቹ ዘንድ የተቃውሞ አቧራ ያስነሳውን መጽሐፍ ነቀፌታዎች ለማብራራትና አንዳንድ ተችዎችንም ልክ ለማስገባት የተፃፈ ይመስላል፡፡
በመጽሐፉ ገፅ 27 ሁለተኛው አንቀፅ ላይ ‹‹መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክን ስፅፍ በኢትዮጵያዊነቴ መንፈስ ተይዤ ነው፤ ይህንን መካድ አልችልም፤ ከሰማይ እንደወረደ ሰው ሆኜ ስለኢትዮጵያ ታሪክ መጻፍ እችላለሁ የሚል ኢትዮጵያዊ ታሪክ ጸሐፊ (ወይም የታሪክ ተመራማሪ) ካለ የሚናገረውን የሚያውቅ አይመስለኝም፤ ከኢትዮጵያዊ ትውልዴ፣ ከኢትዮጵያዊ አስተዳደጌና ስሜቴ፣ ከበርበሬው መፋጄትና ከቡናው ትኩስነት ራሴን ሙሉ በሙሉ አግልዬ ስለኢትዮጵያ መናገር እችላለሁ ብዬ አልዋሽም›› የሚሉት ፕሮፌሰሩ በእኔ ዕይታ የዚህ ዘመን ታሪክ ፅሐፊዎችም እንደ ድሮ ግለ-ታሪክ ፀሐፊዎች (chroniclers) ሁሉ ገለልተኞች (objective) አይደሉም እያሉ ነው የሚል ድምዳሜ ደርሻለሁ፡፡ ስለዚህ መጽሐፉ ከስሜታዊነት አልፀዳም፤ ታሪክ አይደለም፤ ከሽፏል፡፡
በእርግጥ መጽሐፉ እርሳቸው ስለመክሸፍ የሰጡትን ትርጓሜና የክሽፈታችን ማስረጃዎች ናቸው ያሏቸውን ሀሳቦች በጥልቀት ለማብራራት ይሞክራል፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን እንደሚሉት በተለይ ዓድዋ ላይ በዓፄ ምኒልክ ዘመን ድል ያደረግነውና ዓለምን ያስደመምንበት ጣሊያን ከአርባ ዓመታት ዝግጅት በኋላ በዓፄ ኃይለስላሴ ዘመን ከ1928 ዓ.ም እስከ 1933ዓ.ም ድረስ ድል አድርጎናል፤ እኛ ግን በአርባ ዓመታት ውስጥ ከመሻሻል ይልቅ ስንበሰብስ ቆይተናል ይላሉ፡፡ እዚህ ላይ ለፕሮፌሰር ጥያቄ ላንሳ፤ ‹‹ዓድዋ ላይ ጣሊያንን ያሸነፍነው በስልጣኔና በጦር መሳሪያ በልጠነው ስለነበር ነው?›› እንደኔ አይደለም፡፡ ይህ ለፕሮፌሰር ይጠፋቸዋል ብዬ ባልጠብቅም ጳውሎስ ኞኞ ‹‹አጤ ምኒልክ›› በሚል ባሳተመው መጽሐፍ ገፅ 159 ጀምሮ እንዳስቀመጠው ኢትዮጵያውያን ወደ ዓድዋ ዘመቻ ሲሄዱ 42 መድፎች ብቻ ነበሯቸው፡፡ ይህ ቁጥር ከኢጣሊያ ዘመናዊ የተራራ መድፍ ጋር አይወዳደርም ሲልም ይገልፃል፡፡ በሰራዊት ቁጥር ደረጃ በአንፃሩ ኢትዮጵያውያን እጅግ ብዙ ነበሩ፡፡
ጳውሎስ ኞኞ በመጽሐፉ እንዳስቀመጠው የኢጣሊያ ጦር ብዛት ከ20ሺህ የማይበልጥ ነበር፡፡ በኢትዮጵያ በኩል ግን ንጉሠ ነገሥቱ ዓፄ ምኒልክ የመሩት ጦር ብቻ 30ሺህ እግረኛ እና 12ሺህ ፈረሰኛ ነበረው፡፡ ራስ ሚካኤል ደግሞ ስድስት ሺህ አግረኛ እና 10ሺህ ፈረሰኛ ጦር ይዘው ዘምተዋል፡፡ በአጠቃላይ በዓድዋው ጦርነት በኢትዮጵያ በኩል 120ሺህ እግረኛ እና 28ሺህ ፈረሰኛ ጦር ተሰማርቷል፡፡ በሰው ደረጃ ሲቆጠር ዓድዋ ላይ 148ሺህ ሕዝብ ዘምቷል፡፡ በንፅፅር ሲታይ ለአንድ የኢጣልያ ወታደር ቢያንስ ሰባት ኢትዮጵያውያን ተመድበው ነበር ማለት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ያኔ ኢጣሊያን ያሸነፍነው በቴክኖሎጂና በወታደራዊ ስልት በልጠን ነበር ወይ? ካልሆነ የኋለኛው ሽንፈታችን እንዴት ክሽፈት ሊሆን ይችላል? ከዕድለ-ቢስነት ውጭ!
ሁለተኛውን የኢጣሊያ ወረራ ስንመለከት ደግሞ አንድርዜይ ባርትኒስኪ እና ዮዓና ማንቴል-ኒየችኮ ጽፈውት አለማየሁ አበበ ወደ አማርኛ የመለሰው ‹‹የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጄመሪያው እስከ አሁኑ ዘመን›› የሚለው መጽሐፍ ላይ ከገፅ 508 ጀምሮ እንደተብራራው የኢጣልያ ጦር ብዛት ተጠባባቂውን ጨምሮ 500ሺህ ያህል ነበር፡፡ በኢትዮጵያ በኩልም በእርግጥ 600ሺህ ያህል የሰው ኃይል ለጦርነቱ ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ ኢጣሊያዎቹ በዘመናዊ የጦር መሳሪያ፣ ታንክና በበርካታ የጦር አውሮፕላኖች የሚታገዙ የነበሩ ሲሆን ኢትዮጵያውያኑ ግን ከግማሽ የማያንሱት ቆመጥ የታጠቁ ነበሩ፡፡ እንግዲህ በሁለተኛው የኢጣሊያ ወረራ ወቅት የጦር መሳሪያ ቴክኖሎጂዎችን ደረጃ ማወዳደሩን ትተን በሰው ኃይል ብቻ እንኳ ብናወዳድረው ንፅፅሩ አንድ ለአንድ ነበር ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከዓድዋው የአንድ ለሰባት ጥምርታ በጣም ያነሰ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ታዲያ በዚህ ሁኔታ መሸነፍ መክሸፍ ነው ፕሮፌሰር?
ሌላው ለፕሮፌሰሩ ማንሳት የምፈልገው ጥያቄ ከዓፄ ቴዎድሮስ ሽንፈትና ከዓፄ ዮሐንስ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ በመጀመሪያ ግምቴን ሳስቀምጥ ፕሮፌሰር መስፍን ለዓፄ ዮሐንስ 4ኛ ያላቸው አመለካከት ግብዝነት ያለበት (stereotype) ይመስለኛል፡፡ የውጫሌ ውል እ.ኤ.አ ግንቦት 2 ቀን 1889 ቦሩ ሜዳ አጠገብ በምኒልክና በኢጣሊያ መካከል ተፈረመ፡፡ ዓፄ ምኒልክ ውሉን መፈረማቸው ስህተት መሆኑን እ.ኤ.አ መስከረም 27 ቀን 1890 የአንቀፅ 17ን የጣሊያንኛ ትርጓሜ ስህተት መሆን በመጥቀስ ለኢጣሊያ ስህተት መሆኑን በደብዳቤ ጽፈው አሳወቁ፡፡ ውሉን እንደማይቀበሉት ለአውሮፓ መንግስታት ይፋ ያደረጉት ግን አምስት ዓመታትን ዘግይተው ነበር፡፡ ከዚያ ዓፄ ምኒልክ የውጫሌ ስህተታቸውን ያረሙት ስህተቱን ከፈፀሙ ከ8 ዓመታት በኋላ አሁንም በአውሮፓውያኑ መጋቢት 01 ቀን 1896 ዓድዋ ላይ ባስመዘገቡት ድል ነበር፡፡
ነገር ግን ፕሮፌሰር መስፍን ዓፄ ዮሐንስን በመጽሐፋቸው (አዳፍኔ ፍርሃትና መክሸፍ) ገፅ 15 ላይ ሲነቅፉ ‹‹አጼ ምኒልክ በውጫሌ ውል የሠሩትን ስህተት በአድዋ ላይ አርመውታል፤ አጼ ዮሐንስ ግን ከእንግሊዞች ጋር ባደረጉት ውል የተሠራውን ስህተት ማረም አልቻሉም፡፡›› ይላሉ፡፡ አሁንም ጥያቄን ላንሳ፤ ዓፄ ዮሐንስ ከእንግሊዝ ጋር እ.ኤ.አ በሰኔ 03 ቀን 1884 ዓድዋ ላይ የተፈራረሙትን ውል ስህተት ለማረም እንደ ምኒልክ 8 ዓመት ነበራቸው ወይ? ሌላው ጥያቄ ደግሞ እንግሊዞች ቴዎድሮስን ለመውጋትና ዜጎቻቸውን ለማስፈታት ወደ መቅደላ ሲመጡ የተባበሯቸው ብቸኛ የቴዎድሮስ ጠላት ተደርገው በፕሮፌሰሩ የቀረቡት በዝብዝ ካሳ (በኋላ ዮሐንስ 4ኛ) ናቸው፡፡ ፕሮፌሰሩ ዋግሹም ጎበዜን (በኋላ ተክለ ጊዮርጊስ) ረስተዋቸው ነው? ቀደም ሲል አለማየሁ አበበ ወደ አማርኛ መልሶታል ባልኩት የኢትዮጵያ ታሪክ መጽሐፍ ገፅ 282 ላይ እንደተገለፀው እንግሊዞች ወደ መቅደላ ሲገሰግሱ ዋግሹም ጎበዜ 60ሺህ ወታደሮች በስራቸው ነበሩ፡፡ ነገር ግን በእንግሊዞች ላይ ኮሽታ አላሰሙም፤ ለዚህ ውለታቸውም የወቅቱን መዲና መቅደላን በስጦታነት አግኝተዋል፡፡ ታዲያ ፕሮፌሰሩ ስለዓፄ ዮሐንስ 4ኛ ግብዝነት የጀቦነው ጥላቻ ባይኖርባቸው ኖሮ ስለምን እንግሊዞችን የደገፉ ብቼኛ ተጠያቂ ያደርጓቸዋል?
“አዳፍኔ፣ፍርሃትና መክሸፍ›› እርስ በእርስ የሚቃረኑ ሀሳቦችም አሉበት፡፡ ለምሳሌ በመጽሐፉ ገፅ 63 የመጨረሻው አንቀፅ ላይ ‹‹ትምህርት የአዳፍኔ ፀር ነው፤ ስለዚህም አዳፍኔም የትምህርት ፀር ነው›› ይላሉ፡፡ ገፅ 68 መካከለኛው አንቀፅ ላይ ሲደርሱ ደግሞ ‹‹በአጠቃላይ አዳፍኔ ባለበት የትምህርት መሣሪያነት በመጀመሪያ ለአዳፍኔ፣ ቀጥሎም ለቤተ ሃይማኖት ነው፤›› ይላሉ፡፡ መጀመሪያ ነገር አዳፍኔ ለትምህርት፣ ትምህርትም ለአዳፍኔ ፀር ከሆኑ አንዱ ለአንዱ እንዴት መሳሪያ ሊሆን ይችላል? አንዱ ለአንዱ መሳሪያ ሊሆን የሚችለው እኮ በሁለቱ መካከል የለበጣም ቢሆን ፍቅር ሲኖር ነው?
ፕሮፌሰር መስፍን ሲቀጥሉ በገፅ 114 ላይ ‹‹ወደጥሩው ለውጥ የሚወስደውን አቅጣጫ ለመያዝ የማያስችለው ጋሬጣ አዳፍኔ ነው፤ የአዳፍኔ ዋናው ሥራ ጤንነት፣ ዕውቀት፣ ትብብር፣ ብልፅግና፣ ማኅበራዊ ጥንካሬ እንዳይፈጠሩና ሕዝቡ ወይም ሕብረተሰቡ ደካማና ተስፋ ቢስ ሆኖ በቀላሉ ለመገዛት የሚመች እንዲሆን ነው›› ይላሉ፡፡ ለእኔ በገባኝ ልክ ፕሮፌሰሩ ‹‹አዳፍኔ›› የሚሉት ስርዓተ-መንግስቱን ወይም ገዥውን አካል ይመስለኛል፡፡ አሁን ወንዝ በበራፉ ዓመቱን ሙሉ የሚያልፍበት ሰው በንፅህና ጉድለት በሚመጣ በሽታ ቢጠቃ ስለምን አዳፍኔ ተጠያቂ ይሆናል? ወንዝ ዳር እየኖረ ጳጉሜን ጠብቆ የሚታጠብ ሰው ቢኖር ንፅህናውን አለመጠበቁ የግለሰቡ ድክመት እንጅ ‹‹የአዳፍኔ›› እጅ ነው ለማለት ምክንያት የለኝም፡፡ ለብዙዎቻችን እኮ ተንኮልና መጠፋፋትን የሚያስተምሩን ወላጆቻችን ናቸው፡፡ መሪዎችም እንደኛው ሰለሆኑ ወላጆች አሏቸው፤ የወላጆቻቸው የአስተዳደግ ውጤትም ናቸው፡፡ የብዙዎቻችን ወላጆች እኮ የሚመክሩን ‹‹ከጠላትህ ሳይሆን ከወዳጅህ ተጠንቀቅ›› ብለው ነው፡፡ ፀሎታችንም ‹‹አንተ ከወዳጄ ጠብቀኝ፤ ጠላቶቼን እኔ ነቅቼ እጠብቃለሁ›› የሚል ነው፡፡
በአገራችን ያሉ የተለያዩ የፈውስ መድኃኒቶችን የሚያውቁ የባሕል ሐኪሞች በብዛት ነበሩን፡፡ ነገር ግን እነዚህ አዋቂዎች በዕድሜ በጣም ሲገፉ ለአንድ በጣም ለሚወዱት ልጅ ከሚነግሩት በቀር ለማንም ቀርቶ ለሁሉም ልጆቻቸው መድኃኒቱን አያሳዩም፡፡ ይህ ዓይነት ግላዊ የተተበተበ የምቀኝነት አባዜ ባሕል በሆነበት ህብረተሰብ ውስጥ ያደገ አዳፍኔ ያልሆነ መሪም ሆነ ስርዓት እንዴት ሊገኝ እንደሚችል ፕሮፌሰሩ የጠቆሙት ነገር የለም፡፡ በእኔ እምነት ከማኅበራዊ ችግሮቻችን ተኮትኩተው የሚያድጉ ችግሮቻችንን ፖለቲካዊ ያደረጓቸው ይመስለኛል፡፡ አዳፍኔ ሕዝብን ተስፋ ቢስ ቢያደርግ ኖሮ ስለምን በደርግ የጭፍጨፋ ዘመን ሕዝቡ ተስፋ ቆርጦ ፀጥ ረጭ ብሎ አልተገዛም፡፡ እንዲያውም ሕዝብ እንደሕዝብም ተስፋ አይቆርጥም የሚል አቋም አለኝ፤ ተስፋ መቁረጥ የሚመነጨው ከአዕምሮ ስለሆነና የወል የሆነ ሕዝባዊ አዕምሮ ስለሌለ፡፡ አዕምሮ ያለው በግለሰብ ደረጃ ነው፤ ስለዚህ ተስፋ የሚቆርጠውም ተስፋ የሚያደርገውም ግለሰብ ነው፡፡
ሌላው ፕሮፌሰር መስፍን ስለታሪካችን ሲፅፉ በገፅ 117 ላይ ‹‹ማርቲን በርናል የተባለ ሊቅ የተማርነውን ሁሉ ገለበጠው፤ የሴም ቋንቋዎች ከኢትዮጵያ ወደ ባሕር ማዶ ተሻገሩ እንጅ ከዚያ ወደዚህ አልመጡም አለ›› ይሉና ‹‹ባለፉት 27 ዓመታት ውስጥ የበርናልን ፈር ተከትሎ የኢትዮጵያን ታሪክ ተከትሎ የኢትዮጵያን ታሪክ ለመከለስ የሞከረ አንድም ባለሙያ መኖሩን አልሰማሁም፤ የታሪክ ተመራማሪ የሚባሉ ግን አሉ›› ሲሉ ይደመድማሉ፡፡ እርሳቸው እንዳሉት በርናል ጥናቱ የፈጄበት 10 ዓመት ነው፡፡ አስፈላጊና ትክክለኛ ሆኖ ካገኙት የሚያስኬድም ከመሰላቸው ስለምን እርሳቸው ሳይሞክሩት 27 ዓመታትን አሳለፉ? የታሪክ ተመራማሪ ከሚባሉት ውስጥ አርሳቸው የሉበት ይሆን ይሆን?
በነገራችን ላይ የፕሮፌሰር መስፍን አዳፍኔ የአርትኦት ችግሮችም አሉበት፡፡ መጽሐፉ በጥድፊያ የታተመ ይመስላል፡፡ በጥድፊያ አርትኦት ሳይሰራለት ለመታተሙ የሚያሳብቁ በርካታ የፊደል ግድፈቶች አሉበት፡፡ የፊደል ግድፈቶቹን እንተዋቸውና ያልተሟሉ መረጃዎችን እንኳ ለማሟላት ፕሮፌሰሩ ትዕግስት አልነበራቸውም፡፡ ለአብነት በገፅ 129 ላይ ሰንጠረጅ 2 (በሰንጠረጅ 1 ላይ የተመሠረተ) ተብሎ ዓመተ ምህረትና ክፍለ ሀገር (ጠቅላይ ግዛት) የተፃፈበት ነገር ግን ‹‹በሰንጠረጅ 1 ያለው የአርበኞች ስርጭት በመቶኛ›› ተብሎ ባዶ ሰንጠረዥ ታትሟል፡፡ መቼም ይህ ስህተት ለሕትመት ከመቻኮል ካልመነጨ በቀር አይከሰትም፡፡ ወይም ደግሞ ፕሮፌሰሩ ‹‹ከእኔ በላይ ላሳር›› ብለው ለማንም አርታኢ አላሳዩትም ማለት ነው፡፡ ምናልባት እንደርሳቸው በዓፄው ዘመን የተማሩ አርታኢዎች አጥተው ይሆን? እነማዕረጉ በዛብህ የእርሳቸው ዘመን ተማሪዎች አይሆኑ ይሆን?
ወደ መጨረሻ ማንሳት የምፈልገው ነጥብ ደግሞ ፕሮፌሰሩ ‹‹ከእኔ በላይ አዋቂ የለም›› ባይና ዘላፊ መሆናቸውን በመጽሐፉ ማንፀባረቃቸውን ነው፡፡ በመጽሐፋቸው ገፅ 73 ላይ ፕሮፌሰር ባሕሩን እንዲህ ይላሉ፡፡ ‹‹ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ አንድ አስተማሪ ያስታጠቀውን ጉዳይ ይዞ አንድ መጽሐፍ አሳትሟል፡፡›› በተለይ በ‹‹መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ›› መጽሐፍ ላይ አስተያዬት የሰነዘሩ ሰዎችማ የስድብ ናዳ ወርዶባቸዋል፤ ዳግመኛ ለሂስ ብዕራቸውን የሚያነሱም ሆነ አንደበታቸውን የሚከፍቱ አይመስልም፡፡ ብርሃኑ ደቦጭ የተባለውን ተች ‹‹እንግሊዝኛን በአማርኛ ፊደል መጻፍ የሚችል መሆኑን አወቅሁለት›› ሲሉ አጣጥለውታል፡፡ እርሳቸው ታምራት ነገራን ሲወርፉ ከገፅ 214 ጀምሮ ‹‹ፓራግራፍ›› እያሉ እንደጻፉት የሚጽፍ ለማለት ፈልገው ይመስለኛል፡፡ 
ዳንኤል ክብረት በፕሮፌሰር መስፍን ከገፅ 222 ጀምሮ እንደወፍጮ በተደጋጋሚ የተወቀረ ተች ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ‹‹ያውቃል እንዲባል የሚፅፍ እንጅ አውቆ የሚጽፍ አይመስልም›› በሚል ውረፋ የጀመሩት ፕሮፌሰር ‹‹የዩኒቨርሲቲን ዓለም የማያውቁ ሰዎች ሌላ ትርጉም በመስጠት እንዳይሳሳቱ ማስጠንቀቅ ያስፈልጋል፣ በአካል ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሆነው ልባቸው ከደብተራ ተንኮል ላልፀዳም ቀናውን የእውነት መንገድ እንዲያመለክታቸው እመኛለሁ›› ሲሉም አስከተሉ፡፡ ‹‹ይህ ሰው አንብቤአለሁ ሲል በመሀይም ድፍረት ነው›› የሚል ውረፋም ተመርቆለታል፡፡ የዳንኤል ክብረት የዲቁና ማዕረግም በፕሮፌሰር መስፍን ስልጣን ተገፍፏል፡፡ ምክንያት ያሉት ደግሞ ‹‹እኔ እንደማውቀው ዲያቆን ሶስት ደረጃዎች ሲኖሩት የዲያቆኖች አለቃ ሊቀ ዲያቆናት ይባላል፤ አቶ ዳንኤል ሊቀ ዲያቆናትም አልሆነም፤ የአቶ ዳንኤል ዲያቆንነት የቱ ዘንድ እንደሚወድቅና ምን ማለትም እንደሆነ አላውቅም›› ይላሉ፡፡ ዲያቆንነት ሶስት ደረጃዎች ካሉት ዳንኤል ክብረት ሊቀ ዲያቆን ካልሆነ ቀሪዎቹን ሁለት ደረጃዎች ሊሆን እንዳማይችል ግን ፕሮፌሰር መስፍን ግልፅ አላደረጉትም፡፡ በነገራችን ላይ ዳንኤል ብቻ ሳይሆን የዳንኤል ደጋፊዎች የተባሉትም በአዳፍኔ ስድብ ተዳፍነዋል፡፡
የአንተ አሽከር፣ የአንተ ቡችላ፤
ኩፍ ኩፍ ይላል እንደጉሽ ጠላ!
የሚል ስንኝም ተቋጥሮላቸዋል፡፡ ብቻ በአዳፍኔ ብዙ የተዳፈኑ ነገሮችንም አንብቤያለሁ፡፡ ፕሮፌሰሩ እንዲህ ተሳዳቢ መሆናቸውን አላውቅም ነበር፡፡ ከደርግም ሆነ ከኢህአዴግ አባላትም ሆነ ደጋፊዎች አንድም ምሁር ሰው አለመኖሩንም ፕሮፌሰሩ በልበ-ሙሉነት ያስረዳሉ፡፡ ምሁራኑ በአዳፍኔ ተዳፍነዋል፤ አዳፍኔና ዕውቀት ተፃራሪ ናቸውና፡፡ ሁለት ትልልቅ ትምህርቶችንም በአዳፍኔ ፍርሃትና መክሸፍ ውስጥ አግኝቻለሁ፡፡ አንደኛው ኢትዮጵያ ውስጥ ሙስናን ማስቀረት ከባድ መሆኑን፤ ገፁንና ቃላቱን አንድ ባንድ ባላስታውሰውም ‹‹ኢትዮጵያውያን ፈጣሪያቸውን ጭምር በሙስና ውስጥ ለመክተት ስለት የሚሳሉ ሰዎች ናቸው›› ያሉትን የፕሮፌሰር ሀሳብ በጣም ወድጄዋለሁ፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የተራደሁት ነገር ቢኖር ሰዎችን አንድ ባንድ እያነሱ በመሳደብ መጽሐፍ ማሳተም እንደሚቻል ነው፡፡ ሶስተኛ ቁም ነገር ልጨምር ካልኩ ምሁር ለመባል ወይ በንጉሱ ዘመን መማር አሊያ በፕሮፌሰር መስፍን ጽሁፎች ላይ እንደነማዕረጉ በዛብህና ማስረሻ ማሞ የፕሮፌሰሩን ሀሳብ ደጋፊ አስተያዬት ብቻ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ ካልሆነ የዳንኤል ክብረት፣ የኢህአዴግና የደርግ ምሁራን እጣ ፋንታ ገጥሞህ ከ8ኛ ክፍል አላለፈም ትባላለህ፡፡
በመጨረሻም በእርግጥ ይህንን በማለቴ ፕሮፌሰር መስፍን እንደ ዳንኤል ክብረት በስድብ ናዳ መቀመቅ ሊያወርዱኝ ይችላሉ፤ እንደምንም የተማርኳቸውን ሁለት ዲግሪዎችም ወደ ሁለተኛ ክፍል ሊያወርዷቸው ይችላሉ፤ ለነገሩ ከመጀመሪያውም የዚህን ዘመን ተማሪዎች ዕውቅና አልሰጡንም፤ ማን ያውቃል የአዳፍኔ ማዳፈኛ ብለው ሌላ የስድብ መጽሐፍ እንዲጽፉም መነሻ ልሆናቸው እችል ይሆናል፤ ምናልባት ፌስቡክ ላይ እንደኔ አይጣዱ እንደሆነ ደግሞ ላያነቡትና ምንም ላይቀየሙኝም ይችላሉ፡፡ የመጨረሻው ምኞቴ በሆነልኝ እንዳልል ‹‹ይኸው ፈራህ፤ ከሽፈሀል!›› ሊሉኝ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ የፈለጉትን ይበሉ፡፡

የኔ አባት ገበሬው (ሄኖክ የሺጥላ)

የኔ አባት ገበሬው ( ሄኖክ የሺጥላ )
የኔ አባት እሱ ነው አባይ ስር የነቃ
ሃገሩን ያነቃ
አንቅቶ ያለፈ
አልፎ የገዘፈ ።

የኔ አባት ገበሬው
ቃላት እና ዘየው
ዘየና ዝማሬው
ዝማሬና ስራው
የሲና ላይ በትር
ጦሩን ሲነቀንቅ
ቀስቱን ሲያነጣጥር
አነጣጥሮ ሲጥል
የጣለው ሲያጣጥር
እዩት ሲንጎማለል
ዝናር በወገቡ
ጋሻና ጥሩሩ
ኢትዮጵያ ናት ክብሩ !
የኔ አባት ገበሬው
አፈሩን ሲገፋ
ሲገፋ ሲለፋ
ዋሽንቱን ሲነፋ
ነዶውን ሲቀምር
በሮቹን ሲጠምር
ሲወቃ ሲያ-በራይ
አገዳን ከግቻ
ሲነጥል ሲለያይ ።
የኔ አባት ገበሬው
አልቤኑ ነው አልቦው
ሰኔ-ጎሎጎታው ፣ ማረሻና ወገሉ
ግማሽ ጎን አካሉ
ፍቅር ነው እምነቱ
እምነቱ ነው-ቃሉ !
የኔ አባት ገበሬው
አሂዶ ያስሄደ
ጤፍን ያስዘመመ
አደይ ያነጠፈ
ለሀገር እዮሃ ዘርዶ የዘነጠፈ
ግልገል እና ደቦል አጣምሮ ያቀፈ ።
የኔ አባት ገበሬው
እምነቱ ነው ሃብቱ
ፍቅሩ ነው ንብረቱ
ተዋዶ መኖሩ
ተካፍሎ መብላቱ !
የኔ አባት ገበሬው
የኦፊር ስጦታ
የራማ ነጭ እጣን
ሚኒሊክ ሚኒሊክ ፣ የሶሎሞን እጣን
የሰብ’አ ጥር
ውልደትን አብሳሪ
ተጏዥ በጨረቃ
በኮከብ ምልክት ፣ በአምላክ ፍቅር ሲቃ
የኩሽ ምድር ንጉስ የግብጦች አለቃ !
የኔ አባት ገበሬው ነጻነት አይነቱ
የደሙ ቀለም ነው እምቢ ወንድነቱ !
ሞትን የደፈረ
በመድፈር የኖረ
በሕይወት ምልአት
በዜማ ቅኔ ቤት
የተገመደ እውነት ።
ላገሩ ነጻነት
ጥይት ለነብሱ ሕይወት
አ! ብሎ የጠጣ
ጠጥቶ ያለፈ
አልፎ የገዘፈ !
እምቢ ዝባዝንኬ
ዝባዝንኬ ዘኬ
ላገሬ ነጻነት
አባቴ ነው ልኬ
አባቴ ነው መልኬ
እንቢ ! እንቢ ! እንቢ ! እንቢ ! እንቢ !

Ethiopia’s Zone9 Bloggers Head Back to Court After 15 Months Behind Bars

by Endalk | Global Voices
Five members of Ethiopia’s Zone9 blogging collective expect to learn their fate this Wednesday, August 19, when a panel of three judges will meet at Addis Ababa’s Lideta High Court to rule on whether the defendants will walk free or or face another round of trial.
As the 15 months-old botched trial reaches a critical juncture just a few days before the Federal High Court goes on summer recess, we offer a brief summary of the case, along with the proceedings and the possible outcomes of what feels like a never-ending trial.
The case against Zone9
The bloggers of Zone9 covered social and political issues in Ethiopia and sought to promote human rights and government accountability. Known for their critical stance on government policies and practices, they faced various threats before they were arrested in April of 2014, on informal accusations of inciting social unrest via online means. After spending many weeks in pre-trial detention at Maekalawi, an Addis Ababa prison notorious for its harsh conditions, they were charged under the country’s Anti-Terrorism Proclamation.
They now stand accused of terror and treason-related charges for using encryption tools for their online communications and blogging. The Zone9ers’ 21-page charge sheet specifies the laws the regime claims the bloggers have violated since May 2012. Read more on this here and here.
Five of the nine group members originally arrested (one is being tried in absentia) were released on July 8 and 9 of 2015, a few weeks prior to Barack Obama’s historic visit to the country. Authorities dropped all charges against the five, with no formal explanation. No changes have been made to the charges against the four Zone9 bloggers who remain in prison.
Critics suggest that the partial release of Zone9 writers was government’s attempt to deflect mounting criticism about Ethiopia’s dreadful human rights record approaching the Obama visit.
Trial postponed 33 times

The Zone9ers’ trial has been postponed 33 times. Judges have adjourned the case continuously, accepting a panoply of reasons for postponement, ranging from the banal to the bizarre. At a recent hearing, prosecutors pleaded for an adjournment of the case due to what they described as “a shortage of time” to review the case. The judges accepted this as a valid reason, despite the fact that the bloggers have spent more than a year in a prison.

Often times the proceedings were adjourned the moment the defendants set foot in the court room. On some occasions the defendants did not even have a chance to listen to what their counselors said in the court room.
When the government decided to suddenly discontinue the case against five of the writers and let them walk free, the judges did not know about it. Government officials insisted that the five writers were released based on the law of the country, and those who are now free had minimal involvement in the alleged crime. But this sudden move left observers with more questions than answers. Why did the government release just five individuals while keeping the others, when they were all originally charged with the same crime? Will the partial release of the bloggers have an impact on the course of the trial of the others?
What might happen next
A fair trial is all but impossible under the Ethiopian judicial system, which is generally described as dissent-controlling apparatus of the regime. Although the release of five defendants created a short-lived optimism in July, various outcomes are possible on Wednesday. This could include a ruling that amounts to guilty verdicts, another round of long term adjournments, or even an acquittal.
After the partial release of the writers in July, government officials justified their decision to keep the remaining bloggers behind bars, issuing statements containing a wide range of flawed arguments. Those statements could provide the first clear glimpse of how the trial is likely to unfold on Wednesday, not just in terms of immediate decisions of the judges – guilty verdicts or acquittals – but also in terms of precisely how the government intends to release the bloggers.
In a sit-down interview following the Obama visit and televised on the country’s sole TV network, veteran journalist Tefera Gedamu asked Minister of Government Communication Affairs Redwan Hussein, “Why didn’t you release some of them as a gesture of good will… was it not that possible? I know you say there is a due process of law…”
Redwan responded that the government would give pardon and parole when there is a reason to do so. He also defended the partial release of the bloggers, redoubling his indication that the remaining bloggers would not be released, that their case would not be dropped, and that the threat of going back to prison would be hanging over the heads of the released ones as well. He continued:
The level of their offense must be weighed…those which have a milder offense as compared to others, though each and every one of them could be convicted… if they behave and if their release outweighs the public interest …that serves the public interest rather than them staying behind bars, then they will be released.
Tedros Adhanom Minister of Foreign Affairs of Ethiopia also spoke along the same lines as Redwan when questioned by VOA Amharic service.

These statements are indications that the high court will likely uphold the convictions these government officials made in public. However, the statements can also be read to indicate that the government intends to release the bloggers after their conviction through clemency. Whatever the outcome, a robust array of online voices will continue to say #FreeZone9Bloggers until they are all released.

በኢህአዴግ አድናቂ ማብዛት ያስገመግማል!

ሚኒስትሩ ዳያስፖራውን ሲያዝናኑና ሲፈርሙ አመሹ

    የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ (መሬት ይቅለላቸውና!) ፓርቲያቸው ኢህአዴግ ሥልጣን በያዘ ማግስት፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር ለውይይት መቀመጣቸው ይታወሳል፡፡ (ውይይት ሳይሆን ሽንቆጣ ነው የሚሉም አሉ!) 

በእርግጥ ማንም ቢሆን ጠ/ሚኒስትሩ ከምሁራኑ ጋር ይወዳደሳሉ ብሎ ሊገምት አይችልም (የመተኳኮስ እንጂ የመወዳደስ ታሪክ የለንም!) ለነገሩ ምሁራኑም ቢሆኑ ጠ/ሚኒስትሩን በዝምታ አላለፏቸውም፡፡ የቻሉትን ያህል በነገር ወጋ ወጋ አድርገዋቸል ይባላል፡፡ (40ዎቹ የዩኒቨርሲቲ መምህራን የተባረሩት ከውይይቱ በፊት ነው በኋላ?) 
የሆነ ሆኖ ውይይቱ በሉት ሽንቆጣው ከተጠናቀቀ በኋላ ጠ/ሚኒስትሩ የተማሪነት ዘመን ዶርማቸውን የጐበኙ መሰለኝ (ሩብ ክ/ዘመን ስለሞላው ብሳሳት ወይም ብስት አትፍረዱብኝ!) እናላችሁ … ያን ጊዜ ነው ምድረ ምሁር በሰልፍ ጠ/ሚኒስትሩን ሲያስፈርም በኢቲቪ መስኮት የተመለከትነው፡፡ (የታዘብነው ለማለት ፈልጌ ነው!) ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣን … ያውም አድራጊ ፈጣሪ የአገሪቱ መሪ … ድግሪ ለጫኑ አድናቂዎቹ ሲፈርም ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁትና የተገረምኩት ያኔ ነው፡፡ 
ለነገሩ ሁኔታው ለጠ/ሚኒስትሩም ዱብዕዳ ሊሆንባቸው እንደሚችል አያጠራጥርም፡፡ (ድንገተኛ መስሎኝ?!) አልነገሩንም እንጂ ጠ/ሚኒስትሩ በፓርቲያቸው ክፉኛ ተገምግመውም ይሆናል፡፡ (በኢህአዴግ አድናቂ ማብዛት ያስገመግማላ!)
ግን እኮ ኢህአዴግ ብቻ ሳይሆን ደርግም ሆነ ጃንሆይ በአድናቂ ጉዳይ የተለዩ አይመስለኝም (አርፎ የሚገዛ እንጂ አድናቂ ምን ይረባል?) በእነ ምኒልክና አፄ ቴዎድሮስ ዘመን ግን የነበረውን አላውቅም፡፡ 
እኔ የምለው … እንዲያ ተሰልፈው ጠ/ሚኒስትሩን ሲያስፈርሙ ያየናቸው ምሁራን ከአንገታቸው ነው ከአንጀታቸው? (ሃቀኛና አስመሳይ አድናቂ ሊኖር ይችላል ብዬ እኮ ነው!) ከአንገትም ይሁን ከአንጀት ግን ጠ/ሚኒስትሩ በርካታ ምሁራንን አሰልፈው ፊርማቸውን በማኖር የመጀመሪያው የኢህአዴግ ከፍተኛ ሹም ይመስሉኛል፡፡ 
በነገራችን ላይ በዚያን ሰሞን በዚሁ ጋዜጣ “መልዕክቶቻችሁ” ዓምድ ላይ ስለጉዳዩ የወጣ አንድ ፅሁፍ፤ “አድናቆት ነው ማመልከቻ?” በሚል ምሁራኑን በነገር ሸንቆጥ ማድረጉን አስታውሳለሁ። ጠ/ሚኒስትሩ ግን በጋዜጣ ሳይሆን በፓርቲያቸው ተሸንቁጠው ሊሆን ይችላል፡፡ (ኢህአዴግ “ቀናተኛ” ነው አሉ!) የዩኒቨርሲቲ ምሁራንን ድባቅ ለመምታት ሄደው ድንገተኛ አድናቂዎች ማፍራታቸው እንዴት ላያስገመግም ይችላል? (“ከምሁራን ጋር መሞዳሞድ” ተብሎ ይሆናል?) 
ኢህአዴግ ግን ለምንድነው ለግለሰቦች ዕውቀትና ብቃት፣ ምጥቀትና ጥልቀት ዋጋ የማይሰጠው? (ለራሱ ሹማምንት ማለቴ እኮ ነው!) ራሳቸው ጠ/ሚኒስትሩ መወደስ የጀመሩት ካረፉ በኋላ እኮ ነው!! (ማድነቅ በህይወት እያሉ ይሻላል!)
በቅርቡ የኢህአዴግ ሹማምንት እርስ በርስ በተገማገሙ ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከፌስ ቡክ አጠቃቀማቸው ጋር በተያያዘ መገምገማቸወን በወሬ ወሬ ስሰማ (ግልፅ መረጃማ ከየት ይምጣ?!) በግርምት ተሞላሁ። (ሚኒስትሩ በማህበራዊ ሚዲያ “አክቲቭ” ናቸው!) እናላችሁ ግምገማው… “ፌስ ቡክን የራሱን ገጽታ ለመገንባት ይጠቀምበታል” የሚል ነበር አሉ፡፡ ክፋት አለው እንዴ!?) 
እሳቸውም ግን የዋዛ አይደሉም፡፡ በአግባቡ ተከላክለውና ተከራክረው መርታታቸውን ሰምቻለሁ፡፡ (ወንዳታ!) በነገራችን ላይ “የኢህአዴግ ደጋፊ ያልሆንኩ የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም አድናቂ ነኝ” (ፊርማቸው ግን ይቀረኛል!) 
በነገራችሁ ላይ “ኢህአዴግን የማልቃወም የትግል ተወዳዳሪ ነኝ” የሚሉት የቀድሞ የፓርላማ አባል መጨረሻቸው እንዴት ሆነ? ይኸውላችሁ ሚኒስትሩ እኔ ብቻ ሳልሆን ብዙ ሺ አድናቂዎች አላቸው (በፌስ ቡክ ማለቴ ነው!) ሰሞኑን በሚሊኒየም አዳራሽ እየተከበረ ባለው “የዳያስፖራ ቀን” በዓል ላይ ደግሞ ከአንጋፋው ድምፃዊ አሊ ቢራ ጋር ተቃቅፈው አቀንቅነዋል (የአርቲስት ነፍስ ሳይኖራቸው አይቀርም!) 
ሚኒስትሩ ከመድረክ ከወረዱ በኋላም በአድናቂዎች ተከበውና ታጅበው ነበር፡፡ የአገር ዳያስፖራ እየተጋፋ ሲያስፈርማቸው ነበር አሉ። (አድናቆት ይሁን ማመልከቻ… አልተጣራም!) እግረመንገዴን አንድ ጥያቄ ብሰነዝርስ … አሁንም ዳያስፖራው “መሬት በነፃ” እና “መኪና ያለቀረጥ” የሚለውን ጥያቄ አልተወም የሚባለው እውነት ነው እንዴ? (እንድታዘባቸው ስለማልፈልግ እውነት ባልሆነ!)
ወደ ክቡር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እንመለስ። ዶ/ር ቴዎድሮስ በሰሞኑ ተግባራቸው የግምገማ ቢላዋ እንደሚሳልላቸው የሚገመት ነው፡፡ (ልብ ያመነውን ፈጽሞ መገምገም ይሻላል!)
እናላችሁ … አንዳንዱ መድረክ ላይ ወጥተው፣ ማይክ ይዘው መዝፈናቸውን እንደሃጢያት ሊቆጥረው ይችላል፡፡ ሌላው እንደዝነኛ አርቲስት (Celebrity) ለዳያስፖራው መፈረማቸው ላይዋጥለት ይችላል፡፡ (“ከዳያስፖራ ጋር ተሞዳሞደ የሚልም አይጠፋም!) እውነቱ ግን ምን መሰላችሁ? ሚኒስትሩ ዘፈኑም … ፈረሙም… ሥራቸው ነው የሰሩት (የአሰራሩን መንገድ ግን ቀይረውታል!) ያልገባው ደግሞ ይጠይቃል እንጂ ለጭፍን ትችትስ አይነሳም፡፡ እንግዲህ “የዳያስፖራ ቀን” በዓልን ማዘጋጀት የእሳቸው መ/ቤት ሃላፊነት ይመስለኛል፡፡ እናም ዳያስፖራውን እንደ ሚኒስትር እላይ ተሰቅለው ሳይሆን እንደ አማካይ ሰው መሬት ወርደው ተቀበሉት፡፡ አስተናገዱት፡፡ ዘፈኑለት። ፈረሙለት፡፡ ይሄ ደግሞ ልብ ለልብ ያቀራርባል፡፡ ሰዋዊ ስሜትን ይፈጥራል፡፡ ተግባቦትን ያቀላጥፋል። የሥልጣን ግንብን ያፈርሳል፡፡ (ከዚህ በላይ ሥራ አለ እንዴ?)
በነገራችን ላይ እንኳንም አድናቂያቸው ሆንኩ ብያለሁ፡፡ አንድ ቀን ሲገጥሙኝ ደግሞ እንደ ምሁራኑ ወይም እንደ ዳያስፖራው ሳልጋፋ ቀስ ብዬ “ፈርሙልኝ” ማለቴ አይቀርም፡፡ (“አድናቆት ነው ማመልከቻ?” ከሚል ሽንቆጣ ለማምለጥ እኮ ነው!) እንደክቡር ሚኒስትሩ የፓርቲ ግምገማ ባይኖርብኝም የሰው ነቆራ ግን አይቀርልኝም፡፡ በዚህ አጋጣሚ በግሌ ዶ/ር ቴዎድሮስን “የዓመቱ ምርጥ ሚኒስትር” በሚል እንደመረጥኳቸው ለመግለፅ እወዳለሁ፡፡ (“የኢህአዴግ ደጋፊ ያልሆንኩ የሚኒስትሩ አድናቂ” መሆኔ እንዳይዘነጋ!) 
Source: Addis Admass

“በኦሮሚያ ክልል ከ70 በላይ አርሶ አደሮች የብሔር ጥቃት ደርሶባቸዋል” ሰመጉ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ ከ70 በላይ አማርኛ ተናጋሪ ገበሬዎች፣ ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎ ከመኖሪያ ቀዬአቸው መፈናቀላቸውን የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) በሪፖርቱ አመለከተ፡፡ የአንድ ሰው ሕይወት መጥፋቱንም አረጋግጫለሁ፤ ብሏል፡፡ 

ሰመጉ ጉዳዩን ሲመረምር መክረሙን ጠቁሞ፣ “ብሔር ተኮር ማፈናቀልና እንግልት በአስቸኳይ ይቁም” በሚል ርዕስ ይፋ ባደረገው 136ኛ ሪፖርቱ የወረዳው የጸጥታ ሓላፊዎችና ባለሥልጣናት የብሔር ግጭቱን መቀስቀሳቸውን አስታውቋል፡፡ 
እንደ ሪፖርቱ፣ የወረዳው ባለስልጣናትና የፀጥታ ኃላፊዎች አርሶ አደሮቹን፣ “እናንተ የዚህ የአካባቢው ተወላጅ ሳትሆኑ ሀብት እያፈራችሁ የአካባቢው ተወላጆች ግን ከእናንተ ያነሰ ገቢ ነው ያላቸው፤ … ይህን ገቢ ያገኛችሁት በኛ መሬት ነው፤ የክልሉ ተወላጆች ባለመሆናችሁ ክልሉን ለቃችሁ ውጡ፤” በማለት በተለያዩ ጊዜያት ንብረታቸውን በመንጠቅና ለእስራት በመዳረግ እንግልት ሲፈፅሙባቸው ቆይተዋል፡፡ በተለይ መጋቢት 27 ቀን 2007 ዓ.ም አንድ የአካባቢው ተወላጅ ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ የወረዳው የፀጥታ ኃላፊ “ግድያው የተፈፀመው በአማራ ብሄር ተወላጆች ነው” በማለታቸው ግጭት ተቀስቅሶ፤  ሚያዚያ 9 ቀን 2007 ዓ.ም 85 አርሶ አደሮች ለእስራት መዳረጋቸውን፣ የአማራ ተወላጅ አርሶ አደሮች መኖሪያ ቤቶች እንዲቃጠሉ መደረጉን እንዲሁም የታሠሩትን የነዳጅ በሚል 300 ብር ከእያንዳንዳቸው በመቀበል እንደተለቀቁ ሰመጉ አጣርቻለሁ፤ ብሏል፡፡   በግጭቱ የአንድ ሰው ሕይወት ሲጠፋ 10 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ 99 የሳር ክዳን ቤቶችና 25 የቆርቆሮ ቤቶች በእሳት ተቃጥለው መውደማቸውን የዘረዘረው ሰመጉ፤ መኖሪያ ቤታቸው ለተቃጠለበቸውና በተለያዩ ቦታዎች ተበታትነው ለሚገኙ ዜጐች አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ እንዲያገኙ ጠይቋል፡፡ መንግሥትም ለተፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ የተጠናና የማያዳግም የመፍትሔ ርምጃ ከሕዝብ ጋር በመመካከር እንዲወሰድ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ አመልክቷል፡፡ 
Source: Addis Admas

ኢትዩጵያ የዓለሙ መፋረጃ - ስለ ዐምሐራ ህዝብ አሰያየምና ትርጉም - በንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደኢየሱስ


ስለ ዐምሐራ ህዝብ አሰያየምና ትርጉም ልታዉቁት የሚገባ እዉነተኛ ታሪክ ይህ ነዉ ፡፡ በዚህም የታሪክ አጠራር ምክንያት የአገዉ ህዝብ የሆኑት ህምራ ፤አዊ፤ ቅማንት፤ፈላሻና ብሌን ከ13ተኛዉ ክ.ዘ ጀምሮ በክርስትና እምነት መቀበላቸዉና መጠመቃቸዉ
ምክኒያት እንዴት ዐምሐራ ተብለዉ ይጠሩ እንደነበር ያሣያል፡፡ "ዐምሐራ" የሚለዉ ቃል መልእክትና ትርጉም ባለዉ ምክንያት በኢትዩጵያ ምድር ለሚኖረዉ ለአብዛኛዉ የአገሪቱ ነባር ህዝብ የተሰጠ ትዉፊታዊ ስያሜ ነዉ፡፡ ቃሉ ከግዕዝ ተገኝቷል፡፡ በግዕዝ "ዐም" ማለት ሕዝብ ሲሆን "ሐራ" ማለት ደግሞ ነጻ ማለት ሲሆን "ዐምሐራ" የሚለዉ የቃል ለቃል ትርጉም "ነጻ ህዝብ" ማለት ሲሆን ይህም ትርጉም የእዉነተኛ ኢትዩጵያዊን ማንነት ከሚገልጹት ዓበይት ባሕሪያት መካከል አንዱ መሆኑን በግለጽ ያመለክታል፡፡ በአጠቃለይ ቅዱስ ኪዳነ ሃይማኖት እየተማሩና እያወቁ በፈቃዳቸዉ ሲገረዙና ሲጠመቁ ዐምሐራ ወይም ክርስቲያን እየተባሉ የእግዚአብሄር ህዝብ ሆኑ፡፡ በዚያ ጊዜ ያ ግለሰብ ዐምሐራ ሆነ ይባልል፡፡ ነፃ ወገን ሆነ ማለት ነዉ ሲሆን ነፃነቱም ከባዕድ አምልኮ ከዲያብሎስና ከሰዉ ተገዥነት ፤ከኃጢያት ቀንበር ከሞት ባለዕዳነት ተላቅቆ በእግዚአብሄር ልጅነት ለመኖር መብቃት ነዉ፡፡ ቋንቋዉን ፊደሉም ይኸዉ ኢትዩጵያዊ ህብረተሰብ ተስማምቶ የፈጠረዉ ዐምሐርኛ ወይ ኢትዩጵያኛ ይሆናል፡፡ ግዕዝ ራሱን የቻለ ፊደል ያለዉ የኢትዩጵያዉያን የመጀመሪያ እናት ቋንቋቸዉ መሆኑ በዓለም ሕዝቦች ዘንድ ሳይቀር በይፋ የታወቀ ነዉ፡፡ የዐምሐራዉ ኅብረተሰብ መነጋገሪዉ ያደረገዉ ቋንቋ ዐምሐርኛ ተብሏል፡፡ የዚህ ኅብረተሰብ የቃል ብቻ ሳይሆን የጽሕፈት መገናኛዉ ጭምር የሆነዉ ይህ ልሳን ግንድ ቢሆንም በጋብቻና በልደት እንደተዋሃደዉ እንደቋንቋዉ ባለቤት ሁሉ ዐምሐረኛም ብሄር አቀፍ ሁኖ በሃገሪቱ ዉስጥ በሚነገሩት አያሌና የተለያዩ በሆኑ ልሳናት ራሱን ሲያበለጽግ የኖረ ቋንቋ መሆኑ የቃላቱ ቤተ-መዛግብት ያረጋግጣል፡፡ ዐምሐራ የሚለዉ ስም ለምሳሌ አገዉ፤አርጎባ፤አፋር፤ኦሮሞ፤ጉራ፤ጋፋት፤ሓዲያ፤ ወላይታ፤ከምባት፤ ኩናማ ወይም ትግሬ እንደሚባለዉ በየጎጣቸዉና በየክልላቸዉ በየእምነታቸዉና በየቋንቋቸዉ ተለያይተዉና ተወስነዉ በየስማቸዉ እንደሚታወቁት ብሄሮች ወይም ሴማዉያን ፤ካማዉያን ያፌታዉያን ተብለዉ በመላዋ ምድር ተሰራጭተዉ እንደሚኖሩት እንደሦስቱ የሰዉ ዘር የትዉልድ ቅርንጫፎች ይህም ኅብረተሰብ "አንድ ነጠላ ጎሳ ወይም ነገድ ነዉ" ተብሎ ለእርሱ መለያና መታወቂያ ይሆን ዘንድ የተሰጠ ስያሜ አይደለም፡፡ በሌላ አገላለጽ ዐምሐራ የአንድ ጎሳ ወይም የአንድ ነገድ ወይም የአንድ ዘር ወገን አይደለም ማለት ነዉ፡፡ የቃሉ ፍቺ እንደሚያመለክተዉ ዐምሐራ በኢትዩጵያ ምድር የሰፈሩ ፤ከተለያዩ ጎሳዎች፤ነገዶች፤ዘሮች፤ ቋንቋዎች፤ባህሎችና ሃይማኖቶች የተዉጣጡ ወንዶችና ሴቶች እርስ በርሳቸዉ በመጋባት በሥጋ አንድ የሆኑበት ህልዉና ነዉ፡፡ በመንፈስ ቀድሞ በኪዳነ ልቦና ፤ቀጥሎ በኪዳነ ኦሪት፤ በመጨረሻም በኪዳነ ምህረት የክርስትና ተዋህዶ ሃይማኖት ከእግዚአብሄር በመወለድ ስጋቸዉና ነብሳቸዉ እነርሱም ሁላቸዉ በአንድ መንፈስ ቅዱስ ፍጽም አንድ የሆኑበት ህይዎት ነዉ፡፡ በአጠቃላይ ኢትዩጵያዊነት የተባለዉን ዘላለማዊ የህልዉና ዓላማ በሕያዉነት ከግብ ለማድረስ መለኮታዊዉ ጥሪ በፈቃዳቸዉ ተቀብለዉ ለእርሱ በጋራ ቃልኪዳን የገቡና ለሰዉም ሆነ ለዲያብሎስ ተገዢ ከመሆን ነጻ ወጥተዉ በእግዚአብሄር ሕገ መንግስት በእኩልነት ፍትሕ በመምራት እየተዳደሩ እንደ አንድ ቤተሰብ የሚኖሩበት ስርዓት ሃገር ነዉ፡፡ ዐምሐራዉ ከላይ እንደተገለፀዉ የእኒያ እያንዳንዳቸዉ የየግላቸዉ ብሔረኝነትና ጎሠኛነት ፤አምልኮና ልሳን በፈቃዳቸዉ ትተዉ ኢትዩጵያዊነትን ከፍጹም ሁለንተናዉ ጋር በፈቃዳቸዉና በሃይማኖት የተቀበሉ ፤ የኢትዩጵያ ጥንታዉያን ባለገሮች ኅብረተሰብ ስለሆነ ቀጥሎ ባለዉ ሐተታ እንደሚያብራራዉ ይህ ኅብረተሰብ እዉነተኛዉ ኢትዩጵያዉ ሆኖ ለመገኘት በቅቷል፡፡ እንግዲህ ማንኛዉም ግለሰብ ወንድ ሆነ ሴት በዚህ ኢትዩጵያዊነት አምኖ የዚህ ኅብረተሰብ አባል ለመሆን በፍጹም ነፃነት ፈቃደኛ ሲሆን የሚፈጸምለት ስርዓት አለ፡፡ ይኸዉም ከመንፈስ ቅዱስ ህይዎት የሚያበቃዉን ፀጋ የሚጎናጽፍበት ልዩ ስርዓት ነዉ፡፡ እርሱም በሃይማኖት እዉቀት በእዉነተኛ ንስሓ በክርስትና ጥምቀትና በቅዱስ ቁርባን ምስጢራ ይፈጽማል፡፡ ለዚያ ግለሰብ ይህ ስርዓት እንደተፈጸመለት ወዲያዉኑ ያ ግለሰብ ዐምሐራ ሆነ ፤ ክርስቲያ ሆነ ወይ ኢትዩጵያዊ ሆነ ማለት ነዉ፡፡ ዐምሐራነት በኃላ በስጋ ጋብቻ ጭምር እስኪዋሃዱበት ድረስ በቅድሚያ እንዲህ በመንፈስ የሚወለዱበት ስለሆነ ጎሳ ወይም ብሄር አለመሆኑ በዚህ ይታወቃል፡፡ በዚህ ጌዜ ያ ግለሰብ ኢትዩጵያዊነት በሚያስተማምን ቃል ኪዳን ለዘላዓለም የሚያጎናፅፈዉን ያን በመለኮታዊ ፀጋ የተገኘዉን ሰብዓዊ ነፃነት እንዳይቀዳጅ ከልክሎት ከኖረዉ ከጠባብ ብሄረኝነትና ከጎሠኝነት ከቋንቋና ከአምልኮ ባዕድ ቁራኝነት፤ ከአጓል አስተሳሰብም ቀምበር ተላቅቆ ከእዉቀት ብርሃን የወጣለትና የነፃነትን አክሊል የተቀዳጀዉ ኅብረተሰብ አባል ለመሆን የበቃ ይሆናል፡፡ ይህ ዐምሐራ የመሆን ምሥጢር ኢትዩጵያዊ ከመሆን ጋር የሚመሳሰልና እንደ ኢትዩጵያዊነት ሁሉ ያልተቋረጠ ትንግርታዊ ሂደት ያለዉ ሆኖ ኖርዋል፡፡ ዐምሐራ ሆነ ማለት ከላይ እንደተወሳዉ ኢትዩጵያዊ ሆነ እንደማለት ብቻ ሳይሆን በአሁኑ ጊዜ በፍጥረት ዓለሙ ዘንድ በይበልጥ እዉቅና እንዳገኘዉና በመጨረሻ ዘመን የሰዉን ዘር እንደገና አዋህዶ ፍጽም አንድ እንደሚያደርገዉ እንደ አዲስ ኪዳኑ ስያሜ ክርስቲን ሆነ ማለትም ነዉ፡፡ በዚህ መሠረት ዐይነተኛዉ (ማለት አማናዊዉ ወይም እዉነተኛዉ) ዐምሐራ ይህም ዐይነተኛዉ ኢትዩጵያዊ ወይም ዐይነተኛዉ ክርስቲያንም፤ ዐይነተኛዉ ዐምሐራ ነዉ፡፡እንዲህ ከሆነ እነዚህ ሶስት ስያሜዎች ማለትም ዐምሐራነት፤ ኢትዩጵያዊነት እና ክርስቲያንነት በምስጢርና በትርጓሜ ይዘታቸዉ አንድ ሌላዉን ሊተካ የሚችል የተመሳሳይነትና የተወራራሽነት ባሕርይ ያላቸዉ ቃላት መሆናቸዉ በግለጽ ይረጋገጣል፡፡ ለዛሬዉ ኢትዩጵያዊ ትዉልድ የዘር ግንድ የሆነዉ የጥንቱ የዐምሐራ ኅብረተሰብ የኢትዩጵያ ነባር ባለገሮች ከሆኑ ኀዳጣን (ቁጥራቸዉ አናሳየሆነ) እና ብዙኃን ( ቁጥራቸዉ በርካታ የሆነ) ብሄረሰቦች ተዉጣጥቶና ተዋሕዶ የተገኘ መሆኑ ከላይ ተመልክቷል፡፡ የዚህ ጥንታዊ ኅብረተሰብ አባሎች የሆኑት እንያ አባቶችና እናቶች ለቅዱስ ኪዳን አምላክ ለልዑል እግዚአብሄር ፈቃድ ራሳቸዉን በሐይማኖት በማስገዛት ዘላለማዊ በረከትና ፀጋ ለልጅ ልጆቻቸዉ እንደሚያቀዳጅ የተማመኑበት የኢትዩጵያዊነትን መሠረት በበለጠ አጽንተዉ ለመቀጠል በስምምነት የሠጡት ዉሳኔና ዉሳኔዉን በስራ ላይ በማዋል የፈጸሙት ገድል ለዚህ ግዳጃቸዉ ከከፈሉት መስዋዕትነት ጋር እጅግ ብልሆች ፤አርቆ አስተዋዩችና ቆራጦች ለመሆናቸዉ በቂ ማስረጃ ሆኗቸዋል፡፡ እስቲ ዛሬ የትኛዉ ኢትዩጵያዊ ነዉ ወየም ከላይ በጥቂቱ በተወሱትና ከየራሳቸዉ ጠባብ ብሄረኝነት ጋር ተቆራኝተዉ በሚገኑት ጎሳዎች ዉስጥ አባል ከሆነዉ ግለሰብ መካከል እንኳ ሳይቀር የትኛዉ ነዉ እንኳንስ ከአንድ ነጠላ ጎሳ ይቅርና ከሁለት ወይ ከሶስት ጎሳዎች ብቻ የተወልድኩ ነኝ በማለት በሙሉ አፉ ደፍሮ ሊናገር የሚችል? ማንም ሊኖር ከቶ አይችልም፡፡ ምክኒያቱም ያ ኢትዩጵያዊ ወይም የጎሳ አባል ወንድ ሆነ ሴት በወላጆቹ የትዉልድ ግንድ በኩል በጥቂቱ ወደ ኃላ ሄድ ብሎ አያቶቹን፤ የቅድማያቶቹንና የምንዝላቶቹን የዘር ሐረግ ቢስብ ራሱን የኅብረብሄር ፍሬ ማለት አያሌ ጎሳዎች የተዋሃዱበት ቅይጥ ፍጡር ሆኖ ያገኘዋል፡፡ ዐምሐራ ወይም ኢትዩጵያዊ ከሚያሰኙት ዓበይት ባሕሪያት መካከል ደግሞ ይህ የኅብረ ብሄር ፍሬነት አንዱ አይነተኛዉ ባህርይ መሆኑን በትኩረት መመልከት ነዉ፡፡ የዚህ እዉነት አማናዊነትና እርግጠኝነት ባሁኒ ጊዜ በኢትዩጵያ ምድር እንዲሁም በሃገር ዉስጥ በሚኖሩትና በዉጭ አህጉር ተበትነዉ በሚገኙት ኢትዩጵያዉንና ኢትዩጵያዊዉያን ዘንድ ሰፍኖ በሚታየዉ ሁኔታ ጎልቶና ገዝፎ ይታያል፡፡ ይህዉም ዓይነተኛዉ ( እዉነተኛዉ) የዐምሐራዉ ኅብረተሰብ ኢትዩጵያ በእግዚአብሄር መንግስትነት ስር ተዋህዳ የኖረች የማትከፋፈል አንዲት አካል መሆኑን በማመን በጎሳ ወይም በዘር መለያየትን የሚቃወም በመሆኑ ነዉ፡፡ እንዲያዉም ኢትዩጵያዊነት ከዚህ የበለጠና የመጠቀ የጠለቀ ፤የሰፋም ባህርይ አለዉ፡፡ ይኸዉም ለኢትዩጵያ እንዲሁም ላለፉትና ለዛሬዎቹ ወደፊቶቹም ኢትዩጵያንና ኢትዩጵያዉያት ብቻ ላይ ተለይቶና ተወስኖ የተሰጠ፤ እየተሰጠ ያለና የሚሰጥም አለመሆኑ ነዉ፡፡ ስለሆንም ዐምሐራን በመላዉ ዐምሐራ ወይም በሃገር አቀፍ ደረጃ አማራ ክልል ማለት ዐምሐራን ከመሠረታዊ የኢትዩጵያዊነት ባሕር አዉጥቶ እንደ ጎሣ ማስቆጠር የኢትዩጵያ የደም ጠላቶች በሚያዉጠነጥኑት ሴራና በሚያካሄዱት ዘመቻ ዉስጥ ተባባሪ ደጋፊና መሣሪያ መሆን በግለጽ አረጋግጦ የሚያሳይ የክህደትና የአመጽ ተግባር በመሆኑ ነዉ፡፡ ስለዚህ ዐምሐራ ኢትዩጵያዊነትን ሕያዉ ለማድረግ ለመጠበቅና ለማስፋፋት በድርጅታዊ ሆነ በብሄራዊ ደረጃ የሚታየዉን የተዛበ አሠራርና ጉዳይ የሚመለከታቸዉ ወገኞች በሙሉ በብሩቱ አስበዉበት ስለ እዉነተኛ ኢትዩጵያዊነት ዐምሐራ ማስተካከልና ማብቃት ይገባቸዋል፡፡
አማራ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ አማራ ዐማራ የሚለዉን ቃል ብዙዎች የተለያየ ግን ተዛማጅ የሆነ ትርጉም ይሰጡታል፡፡ ከነዚህም መካከል አለቃኪዳኔ ወልድ ክፍሌ- ነጻና ጨዋ ህዝብ ማለት ነዉ ሲሉ ከሳቴ ብርሃን ተሰማ ጨዋ፣ የተመረጠ፣ ነጻ ሕዝብ፤ትርጉሙም አም-ሕዝብ፤ሀራ(ሁር) ምርጥ፤በጥምሩ ዐምሀራ ማለት-ነፃ ሕዝብ፤ በራሱ መገዛት እንጅ የሌሎች ተገዠ የማይሆን ሰዉ ይላሉ፡፡ ሀድሰንና ተከስተ ነጋሽም ዐማራ ማለት ክርሲቲያን ወይንም የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ የሆነ ማለት ሲሆን ዐማሮች ቀድመዉ ክርስቲያን ስለነበሩ በኃላ እስላሞችና ጋሎች ሲመጡ ዐማራ ማለትን ክርስቲያን ማለት አድርገዉ ተቀበሉት ይላል ፡፡ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያምም የእብራይስጥ ሀገር ጎብኝዎች ከብዙ ዓመታት በፊት ኢትዮጵያን በጎበኙ ጊዜ ተራራ ላይ የሚኖር ህዝብ አዩና በእብራይስጥ ቋንቋ ዐማራ ብለዉ ጠሩት ይላሉ፡፡ ይህም በዕብራይሥጥ አም -ሕዝባ ሃራ -ተራራ ማለት ስለሆነ በጥምሩ ዐማራ ሲሉ ተራራ ላይ የሚኖር ደገኛ ሕዝብ ማለት ነዉ ይላሉ፡፡ እንደሳቸዉ ትንታኔ ከሆነ ደገኛዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ በቋንቋዉ ቢለይም የአንድ የዐማራ ሕዝብ ክፍል ነዉ ወደሚለዉ ይወስደናል፡፡ይህ ከሆነ ደግሞ አሁን ባለንበት 88%(88 በመቶ) የኢትዮጵያ ህዝብ በደጋዉ ያገራችን ክፍል ኗ ሪ በመሆኑ 88 በመቶ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዐማራ ነዉ ያሰኛል፡፡ወይም ቀሪዉ 12ፐርሰንት የኢትዮጵያ ሕዝብ ዐማራ አይደለም ማለት ይሆናል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ዐማራ ማለት ምን ማለት ነዉ ? የአማራ ብሄር አለ ወይ ? የሚሉ ጥያቄዎች አሁን በብዙዎች ዘንድ እየተነሳ ያለ ጥያቄ ሆኖአል፡፡ አንዳንዶች እንዲያዉም የዐማራ ሕዝብ እንጅ የዐማራ ብሄር የለም የሚለዉን ሃሳብ በማጣመም ዐማራ የለም የሚል መሰረተ ቢስ ተረት ጀምረዋል ፡፡ ሌሎች ደግሞ የዐማራዉን ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት በመቀነስ አማረኛ ተናጋሪዉን የኢትዮጵያ ሕዝብ እያለ የለህም ለማለት እሽቅድምድም የጀመሩ ይመስላል፡፡ ወያኔ ስልጣን ከመያዙ በፊት በዓለም ይታወቅ የነበረዉ የዐማራዉ ሕዝብ ብዛት በ1990 እንደ Britannia world data 37.7ፕርሰንት ሲሆን ፤የኦሮሞ ሕዝብ ደግሞ35.3ፐርሰንት እንዲሁም በሌላ መረጃ በ1980-84 የህዝብ ቆጠራ ዐማራዉ38ፐርሰንት የኦሮሞዉ ሕዝብ ደግሞ 35.3ፐርሰንት ነበር (copy 1990 pc Globe Tempe AZ, USA) እንደ1984 ዓመተ ምህረቱም የኢትዮጵያ መንግስት ባወጣዉ የሕዝብ ቆጠራ ደግሞከ 52383100 ሕዝብ ዉስጥ የአማረኛ ቋንቋ ተናጋሪዉ (ከኤርትራና ትግራይ)ሕዝብ ጨምሮ 32 ፐርሰንት ነበር፡፡ ሆኖም ወያኔ ስልጣን ከያዘ በኃላ CIA የዐማራን ሕዝብ ከትግረኛ ተናጋሪዉ(ከኤርትራና ትግራይ) ሕዝብ ጋር ጨምሮ 32 ፕርሰንት ነዉ ሲል አወጣ፡፡ (The Swedish institute of international affairs no.2 1993) አማረኛ ተናጋሪዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰለሞናዊ ስርወ መንግስትን ከመሰረተ በኃላ ንጉሶቹ አንድ ባላባት ወይም መስፍን በሸፈተ ቁጥር ከምስራቅ ወደ ምዕራብ ፤ከሰሜን ወደ ደቡብ ከደቡብ ወደ ምስራቅ ወዘተ በመዘዋወር አርፍዉ እንኳን የተቀመጡበት አንድ ማዕከላዊ ከተማና ቤተ መንግስት በቅጡ ሳይገነቡ የሀገርን ድንበር እና የህዝብ አንድነት ለማስጠበቅ የተረከቡትን ሃላፊነት አክብረዉ በጦር ሜዳ ያለፉበት ዘመን ብዙ መቶ ዓመቶች ናቸዉ፡፡ በዚህ ወቅት ከዚያ አካባቢ በምርኮም ይሁን በፍላጎት በወታደርነት የገቡ ወይም ክርስትና ሃይማኖትን የተቀበሉት ዐማሮች የሆኑ ሲባል ፤ንጉሱን ተከትለዉትም ሄደዉ የንጉሱን ስርዓት ለማስጠበቅ ሆነ ወይም በምረኮ በዉዴታም ሆነ ወይም በሆነ ምክንያት በአካባቢዉ የቀሩ ዐማሮች ደግሞ ከአካባቢዉ ጋር ተጋብተዉና ተዋልደዉ ከግዜ ብዛት የሕዝቡን አኗኗር እና ቋንቋ በመልመድ የአካባቢዉ ሕዝብ አካል ሆነዉ ለብዙ ዘመናት ኖረዋል ፡፡ በዚህ መነሻነት አማራ ኢትዮጵያ ዉስጥ በሁሉም ቦታ አለ፡፡ የኢትዮጵያ ያልሆነች ኢትዮጵያ የለችም፡፡ የወያኔ አልበቃ ብሎ አንዳንድ ቀዠቃዣ የፖለቲካ ሰዎች አወቅን እያላችሁ አማራ ምናምን እያላችሁ መቀባጠራችሁን ብታቆሙ
መልካም ነዉ፡፡ . አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል እንዲ


ኢትዮጵያ በተለያዩ ፀሃ•ፍት ዘንድ በተለያየ አጠራርና ስም ስትጠራ ኖራለች:: በዋናነት በኦሪት ላይ "ኩሽ" ትባል ነበር:: እንግዲህ ከዚህ በኋላ ነው 70 ሊቃውንት በጋራ ሆነው ብሉይን ከእብራይስጥ ወደ ፅርዕ/ግሪክ/ ሲተረጉሙ "ኩሽ" የሚለውን ቃል ከግብፅ በስተደቡብ ያለውን አገር ሁሉ ለመጠቆም ይጠቀሙበት የነበረውን የነገድ አባት ስም("አይቶ ፒያ") ወይም "Aithio-Pia" ብለው ተረጎሙት:: ይህን ወደ ግዕዝ ሲተረጉሙትም ቃሉን ብቻ እንደወረደ "ኢትዮጵያ" ብለው አሰፈሩት:: ከግዕዝ ወደ አማርኛ ሲተረጎምም እንደገና ያለ ፍቺ ሆሄውን ብቻ "ኢትዮጵያ" አሉት:: ህዝቡን ደግሞ "ኢትዮጵያዊ" :: የቃሉ ስር መሰረት የት ነው ? ሲባል ግሪክ ሆነ::ትርጓሜውስ ? ተብለው ሲጠየቁ "በፀሐይ የጠቆረ፣ በፀሃይ የተቃጠለ ፊት ያላቸው.." ብለው ነገሯቸው/ዋሹዋቸው::
እንግዲህ ብሉይ ከሂብሩ ወደ ፅርዕ በተተረጎመበት ዘመን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በፊት በ282 ላይ ነበር:: Aithio - Pia የሚሉት እነዚህ ሁለቱ ቃላቶች "አይቶ" ጥቁር፣አደረገ፣አቃጠለ፣ የሚል ትርጉም ሲሰጥ "ኦፕያ" ወይም "ኦጵስ" ፊት የሚል ትርጉም ይይዝና ነዋሪዎች ፊታቸውን ፀሃይ ያቃጠለው በሚል ፀና:: አንዳንዶችም ሲራሩልን "ጠይም" ለማለት ነው ይሉናል:: እንዴት ግሪካዊያን ኢትዮጵያ ማለት "በፀሃይ የጠቆረ" ማለት ነው እንዳሉን እና እንዳታለሉን/እንደዋሹን ይህን ያህል ካየን ይህን ቀልማዳነት ደግሞ እንዲህ እናፈርሰዋለን::
ኢትዮጵያ ማለት በትክክለኛው፣ ፍጹም በጠራው አገላለጽ ባሁኑ "ኢት-ዮጵ": የአማርኛ አባት በሆነው በግዕዝ = "ኢትኦጵግዮን" የግዕዝ አባት በተባለው በሳባ = "እንቅዮጳዝዮን" ቋንቋ ከመከፋፈሉ በፊት በኖኅና በቤተሰቦቹ ዘመን ኩሽቲክ ሴሚቲክ ተብሎ ከመከፋፈሉ በፊት የነበራት ስያሜ "እንቅዮጳዝዮን" የተባለች አገር ናት:: ስለዚህ በአማርኛ ኢትዮጵያ እያልነው ያለነው በዘመን ብዛት ተወራርሶ እዚህ ደረሰ እንጂ በጥንታዊ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አንድ አይነትና ተመሳሳይ፣ቢገለባበጥ ይዘቱንን የማይለቅ፣በራሱ በፈጣሪ የተሰየመ፣ከነወንዙ የተሰጠ ስያሜ ነው::
+++ "ኢትዮጲስ 1ኛ" እና "ኢትዮጲስ 2ኛ" የሚለው ስም ግሪክ ከመታወቋ ሺ አመት ቀድሞ እዚህ(ኢትዮጵያ) የነገስታት መጠሪያ ስም የነበረ ነው:: "ኢትዮጲስ" በአማርኛም፣በግዕዝም፣በሱባም፣ በእንግሊዘኛም፣ በምንም ቢለዋወጥ ያው "ኢትዮፒስ" ነው:: የአገሪቱ ስም ከግሪክ ብቻ ከተገኘ ንጉስ ኢትዮጲስ ከግሪክ የወሰደው ስም ነውን ? የግዕዝ ቋንቋ በአጋዝያን ዘመን ነበረ:: ኢትዮጵያም ቋሚ ስም፣ ትርጉም ያለው ስም ነበራት:: ምንጩም ፍንጩም ግሪክ አይደለም!!!
ሀበሻ ቆሻሻ መጣያ ማለት ሲሆን ፤ ኢትዮጵያ ደግሞ ያማረ ፣ የተዋበ ማለት ነው። ETHIOPIA = UTOPIA = ጦቢያ ቃሎች ይወራረሳሉ በተለያየ የዓለም ቋንቋዎች። ምንአልባትም ትንሽ የትርጓሜ ልዮነት ሊኖር ይችላል። ግና በደንብ ከተስተዋለ የቃሎቹ ትርጉም ከአንድ ቤተሰብ ይወለዳሉ። ለምሳሌ ያክል ሀበሻን ብንወስድ እንደሚከተለው ይተረጎማል፦ በአረብኛ አባሽ ማለት የተዘበራረቀ፣ አንድ ወጥ ያልሆነ፣ ቆሻሻ የሚገኝበት ቦታ ሁሉ በዚህ ቃል ሲሰየም በእንግሊዘኛ ደግሞ አባሽ ( ABASH ) የሚል ቃል እናገኛለን። ትርጓሜውም annoy, confuse, crush, discomfit, discompose, disconcert, disgrace, dismay, displease, disquiet, dissatisfy, embarrass, humiliate, irk, irritate, mortify, peeve, perturb, shame ማለት ነው። ሀበሻ ወይም በጥቅሉ ቆሻሻ ማለት ሲሆን አረቦች በ624 ዓ/ም በ “ብድር ጦርነት” ጌዜ ፥ ቅድስት እናታችንን መልእክተኛው ልጃቸው ሞሀመድ ትረዳ ዘንድ በፈጣሪ አምላክ ታዛ፣ በ40ሽ ሐረኞች ልጆቻቸውን ክፉኛ ስለተሸነፉ ነው ሀበሽ ፦ ጥርቅምቅማም፤ ታሪክ የሌለው ፤ ቆሻሻ ብለው የጠሩን። ይኸውም እንደነሱ ተመሳሳይ ቀለምና ጠጉር ስላላዩብን ነው። በተጨማሪም በ16ኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ አይሁዶች ከኢትዮጵያ ምድር ሲባረሩ አንወጣም ያሉትን ደግሞ እንግልትና ሲደርስባቸው በተንኮል አቢሲኒያ ( Abyssinia )። ቃሉ ቀጥታ ይተገኘው ከAbyss ነው። ትርጓሜውም የስቃይ ቦታ ማለት ነው። ለዚህ ተቀራራቢው ቃል በአማርኛ “አበሳ” ሆኖ እናገኘዋልን። ስለዚህ በኢትዮጵያ ጠላቶች አትታለሉ አትመኑም እራሳችሁን ለጥፋት አታሰናዱ!! በጥቂት አጋንንቶች አውሮጳውያን፣ የኢትዮጵያን ቅዱስነትን ለማጥፋት የለጠፉብንን ሰይጣናዊ “ኩሽ = “ugly & shit” (ለኩሲ ፣ የሴም ልጅ ነው። ኩሲ የቅዱሳን ቅዱስ ማለት ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ወይም የኔንሮድ ወዘተ አባት ናቸው። የኢትዮጵስም* አባት ናቸው። የኢትዮጵያም ስም የተገኘው ከዚሁ የአባታችን የዘር ሐረግ ነው እንጂ ቃሉ ከግሪክ ተገኘ በማለት በሀሰትና እውነተኛ ታሪካችንን ለማዳከም ብሎም ለማጥፋት ያቀነባበሩት ሴራ ነው። እንዴው ለመሆኑ ማን ነበር የዚህ ዓለም የመጀመሪያዎቹ ስልጡን? የታወቁት የግሪክ ፊሎዞፈሮች** ትምርታቸውን የቀሰሙት በየትኛው ምድር ሆነና ነው? መላው የአፍሪካ ኢትዮጵያ ተብሎ ይጠራ ነበር። እግዚአብሄር ሲፈጥረን አሳምሮ እንጂ መልካችን ተቃጥሎ አይደለም።
የምድር ሁሉ ቋንቋ፣ፈጣሪ ከፍጡሮቹ በተነጋገረበት ቋንቋ "እንቅዮጳዝዮን" ስትባል ቆየችና ቀስ በቀስ "ኢትዮጵግዮን" መባል ጀመረችና በመሐል ቤት ተሰረቀች:: ከዚያ በኋላ ለሌላ ግልጋሎት ሲጠቀሙበት ኖረው ብንፈልግ፣ብንፈልግ፣ብንዳብስ፣ብንዳብስ አጣነው:: በመጨረሻ "ኢትዮጵ" ሆኖ አገኘነው:: "ኢት" = ስጦታ "ዮጵ" = ብጫ ወርቅ ወይም እንቁ "ግዮን" = ፈሣሽ ወንዝ በጥቅል "ኢትኦጵግዮን" = "የግዮን ወርቅ ስጦታ" ከዚያ በፊት ማን ትባል ነበር ? "እንቅዮጳዝዮን" እውነቱ ይሄ እና ይሄ ብቻ ነው! ሙሉው ምንጭ የተገኘው: "የኢትዮጵያ የ5ሺ ዓመት ታሪክ ከኖኅ እስከ ኢህአዴግ " ከሚለው መጽሐፍ በጋዜጠኛ ፍስሐ ያዜ ካሣ የተጻፈ! መጽሐፉ በሚያስደስት መልኩ ሃተታውን እያተተ እና ድምዳሜውን እየደመደመ ይሄዳል:: እኔ ግን ለጊዜው ይበቃል ያልኩቱን ብቻ ነው
ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ከግሪክ ሊገኝ አይችልም ምክንያቱም እንደሚከተለው፦ ፩ ከዓለም መጀመሪያዎቹ ከፍጥረት ጀምሮ እስከ መጀመሪያ የሰው ልጅ ስልጣኔ ኢትዮጵያ ቀዳማዊነትን ትይዛለች። ስለዚህ ግሪኮችን እኛ ኢትዮጵያውያን ማንነታችንን አስተማርናቸው እንጅ እነርሱ አላስተማሩንም። የታወቁን ፊሎዞፎሮችንም ጨምሮ ትምህርታቸውን የገበዩት በኢትዮጵያ ምድር ነው!! ፪ የኢትዮጵያ ስም የተገኘው ከኢትዮጲስ ከሚባለው የኩሲ ልጅ ነው። ትርጓሜውም እጂግ ያማረ የተዋበ ደስ የሚል ለሰብዓዊም ይሁን ለአእምሮ እርካታን የሚሰጥ ሁሉ ኢትዮጵያ ፣ ዮቶፕያ ወይም ጦብያ የሚባለው። ለዚህም ነው ኢትዮጵያ የምድር ገነት የምትባለውም። ኢትዮጵያም በእለ ቅእቡላን (ALKABULAN) ትታወቅም ነበር። መላው የ"አፍሪካ" ተብዬው አህጉር በኢትዮጵያ ይጠራም ነበር እስከ 1884 እ/አ። እለ ቅእቡላን = በምድር ገነት የሚኖሩ ቅቡአን ፈጣሪያቸውን የሚፈሩም ማለት ነው። ፫ እግዚአብሔር ሲስራን አስተካክሎና አሳምሮ ሲሆን ጠቆር ያለ መልክ እንዲኖረን የሆነበት ምክንያት የፀሀይን ጨረር (uv) ለመከላከልም እንዲሁም ሰውነታችን ይሚያስፈልገውን uv ተቀብሎ ለአጥንታችን ጥንካሬ ጤነኛ እንድንሆን ነው እንጂ እንደ እነሱ አመልካከት የኢትዮጵያን ምነት ለማጥፋት ከተነሱት የሰይጣንች ቡችላዎች እንደሚያናፍሱት ወሬ አይደለም። እንደትርጓሜው ከሆነማ ሳንወለድ ገና ነጫጭባ በሆንን ነበር።
*ኢትዮጲስ = ግዕዝ ነው ትርጓሜውም ያማረ ማለት ነው። **ፊሎሶፊ = ግዕዝ ነው ትርጓሜውም ፈልሳፊ ማለት ነው።
• February 18

History 101: Fiction and Facts on Oromos of Ethiopia

(a guide for foreign journalists on Oromos and Ethiopian history)
By Prof. Feqadu Lamessa for Salem-News.com
July 29, 2013, ADAMA, Ethiopia (Salem-News) – Recently, the Qatar-based media al Jazeera has published several articles concerning the Oromo people of Ethiopia. It is the first international media outlet to extensively report on our people and it should be praised for bringing our cause to the world stage.
One of the benefits of this exposure is it forces Ethiopian authorities to address human rights abuses in the country and to let them know that the world is watching. Oromos and other Ethiopians have been struggling for equal rights and democracy for decades. While it is important to report about Oromo people’ background and historical perspectives, it is however vital that we report accurate information. Instead of benefiting us, reporting inaccurate or biased information can actually harm our struggle for democracy. Instead of creating national consensus and peace, it can instigate bitterness and anger.


One of the reasons al Jazeera reported inaccurate information about Oromo history is because it depended on one-sided sources, especially from members or supporters of Oromo groups outside of Ethiopia (diaspora OLF, OFDM etc). But nobody can blame al Jazeera media because most people inside Ethiopia would be too scared to speak or contribute. The only option al Jazeera or any foreign media has is to use diaspora/refugee/external sources outside Ethiopia. This is a dilemma all foreign media outlets face while reporting about third-world countries like Ethiopia.
For educational purposes, some corrections are provided below to fix inaccuracies reported on al Jazeera media regarding Oromo history and our struggle for democracy. The corrections below are supported by non-political scholars, but they might be rejected by biased politicians (both from ruling party and from opposition party) for the obvious reasons. However, they are based on historical textbooks, European authors and scholarly accounts.
Fiction #1:
“Between 1868 and 1900, half of all Oromo were killed, around 5 million people”
Fact #1:
This is one of the most repeated inaccuracies, usually told by Secessionist Oromos, radical ethno-nationalist politicians outside the country or pro-OLF history revisionist websites like gadaa.com et al. However, the undisputed fact is that even the total Ethiopian population (the sum of dozens of ethnic groups) was much less than 5 million in the late 1800s, let alone one ethnic group being 10 million. So claiming that 5 million ethnic Oromos were killed by Emperor Menelik’s forces does not add up. The truth is several thousand Oromos were in fact killed during battles of that era. It was not a “genocide” as some politicians claim but it was a massacre of the ill equipped southern forces defeated by the Shewan military of Emperor Menelik which had more European weapons. Throughout those decades, the truth is more Oromos were killed by other Oromos than by non-Oromos because competing Oromo Clans often traded for weapons to have an upper hand against their local competitors, who were often their fellow Oromo and Sidama neighbors.  And it was not the first lop sided victory of that era in Africa because various communities from all corners of Ethiopia had attacked one another during the “resource battles” and whichever group had more modern weapons had the upper hand. To summarize, Professor Mengistu Paulos of Jimma University said it best when describing right-wing Oromo liberation philosophy:–
“Most fictional accounts of ‘Oromo history’ blindly accepted as facts by some misled people are manufactured by former politicians turned Pseudo-historians like OLF writer Asafa Jalata, who is renowned for abuse of paraphrasing, often with out-of-context citations. For example, while quoting the 19th century Russian Alexander Bulatovich (who provided an ‘educated guess’ of annihilation of almost half Ethiopian population by disease, famine and war, including internal conflict between Oromo clans and with Abyssinians), the OLF-writer Asafa Jalata infamously claimed half Oromo population was killed by ‘evil’ Amharas. This was purposely done by Mr. Jalata to create a foundation for ethnic hatred between Oromos and Amharas. Ironically, even Mr. Bulatovich himself never had the capacity nor the legitimacy to do a reliable census, as he spent just a couple of months walking around Oromia and hunting elephants in 1890s.”
Fiction #2:
“…. largely Muslim Oromo people”

Fact #2:
This is a phrase seen in some media outlets but not most. Oromo people have never been a predominantly muslim people. In fact, both Christianity and Islam is not our ancestral religion because we have practiced an indigenous traditional religion for centuries before. Gradually, Islam and Christianity were both adopted (during Oromo migrations) by us and imposed (during conquest of our lands by Abyssinian/Christians & Somalis/Islam)  on us thru out history. Even today, both the two major religions have equal representation among Oromos. The latest official 2007 census showed that around 48% of Oromos practice Christianity (Both Orthodox & Protestant) while around 47% of Oromos practice Islam. Yet, word on the ground is that the Islam population might soon surpass Christianity among Oromos in the future because Orthodox Christianity is decreasing inside Oromia.

Fiction #3
“Abyssinians labelled Oromos the derogatory word ‘Galla'”

Fact #3:
For many decades, this false statement has been used by Oromo separatists to create emotional resentment among Oromos against Semitic Abyssinians (Amharas, Tigrayans and Gurages).  The fact is the derogatory word “Galla” was first used by Arab and muslim Somalis to describe Oromos as “gal” meaning “outsiders” and “Pagans.” Muslims used this label during Oromo migration because Oromo people had their own religion which the Muslims believed was paganism. Nonetheless, this derogatory word was gradually adopted and used by other Ethiopians.

Fiction #4:
“Oromos were colonized by Emperor Menelik”

Fact: #4
Another popular claim made by secessionist Oromo politicians (and usually repeated by foreign journalists) is the fiction that Oromo people (as a whole ethnic group) were colonized by another ethnic group. Usually, the slogan goes “Abyssinians colonized Oromos” etc. This claim is popular among the Oromo Liberation Front (OLF) organization and consequently among some Diaspora Oromo nationalists living in America and Europe.  While a different version or a re-arrangement of the wording might still be true…in general, the Oromo nation as a whole was never colonized by another Ethiopian ethnic group. To start with, even a united one Oromo nation did not exist at those times. All non-political historical textbooks show the existence of battles between multi-ethnic BUT monolingual communities for many centuries through out Ethiopia. Even in northern Ethiopia (traditional “Abyssinia”) Oromos have migrated and mixed so much with Tigrayans, Amharas, Afars etc for centuries that the “Abyssinia” state itself was never a one-ethnic state. In fact, even around the 1700s, Rayya Oromos and Yejju Wallo Oromos conquered and dominated a portion of Amharas and Tigrayans; and thus made Afan Oromo the official language of Abyssinia for that brief period. Meaning: clans and ethnic groups have mixed up in Ethiopia for over a millennium but the dominant ethnic group always imposed its language since it was convenient. This linguistic domination however was not always as exploitive and as vilified as it is today; because many of the ethnic groups living along trade centers and trade routes often spoke the languages of other ethnic groups already, because there was financial or commercial incentive to do so. This is the background of the region. Therefore, when it comes to the Emperor Menelik era, all historians have argued that it is more factual to say a predominantly Amharic language speaking community gradually conquered a predominantly Afan Oromo language speaking community in the 1800s. So this does not mean an Oromo ethnic group was conquered by an Amhara ethnic group. In fact, just like Amharas of the north were divided,Oromos were also divided and in conflict among themselves. The obvious evidence for this comes from the fact that the Amhara Emperor Menelik was imprisoned by other Amhara regional kings when he was younger. And when he was freed, Oromo clans were also in fierce battles amongst each other, so much so that the Tullama Oromo, Limmu and Macha Oromos created an alliance with the Shewan Amharas of Menelik, leading to the infamous battles of 1880s that led to this said alliance easily crushing the non-allied Oromos in various bloody wars. In short, Oromos as a one whole were never colonized by exclusively non-Oromos. In fact, the original founders of the OLF organization themselves never believed it so they did not emphasize the word “colonization” in the beginning. But in the mid-1970s, OLF leaders needed to mobilize Oromos against Emperor Haile Selassie (who was half Oromo himself) and to justify the call for “Oromia independence” from “colonial Ethiopia.” Therefore OLF had to create a bad cop-good cop scenario for their convenience and simplified history for their people to create national resentment. This helped OLF to portray Oromos as suddenly being colonized by this foreign ethnic group (Amhara) that we (Oromos) have never came in contact with before.  This is common tactic used by national liberation movements around the world. The truth that most Ethiopians know is that Shewa based Oromos and Amharas (ethnically mixed Ethiopians) were the main creators of modern Ethiopia. In his book “Who are the Shoans,” the historian and anthropologist, Dr. Gerry Salole once summarized that: “In terms of descent, the group that became politically dominant in Shewa (and subsequently in Ethiopia) was a mixture of Amhara and Oromo.”

In Conclusion, the above are 4 of the main issues that create confusion for foreign journalists who report on Oromo people and Oromo politics in Ethiopia.  While it is vital that al Jazeera and other media outlets cover the current suffering of Oromos and other Ethiopians, it is necessary to report responsibly. Otherwise, creating confusion and resentment between the younger Ethiopian population causes more problems than solutions. In reality, not just Oromos, but all Ethiopians have suffered under several governments and the only way they can achieve freedom and lasting democracy is when united, not when divided by tribes or not when being polarized by historical lies presented as truth.  It is important that foreign media outlets make corrections or report accurate information to avoid inflammatory statements that are destructive and counter productive against Oromos and all Ethiopian people’ ongoing struggle for democracy, development and justice.

Feqadu Lamessa is a former Adama University professor and writer.

ኢንጂነር ይልቃል ሰማያዊ ፓርቲን በድጋሚ ለመምራት ይወዳደራሉ

ሰማያዊ ፓርቲን ከምሥረታው ጀምሮ ላለፉት ሦስት ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ሲመሩት የነበሩት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ ፓርቲውን ዳግም ለመምራት ራሳቸውን ዕጩ ማድረጋቸውን አስታወቁ፡፡ፓርቲው ከተመሠረተ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያካሂደው ጠቅላላ ጉባዔ በመጪው ነሐሴ 16 እና 17 ቀን 2007 ዓ.ም.
የሚካሄድ ሲሆን፣ በወቅቱ በሚካሄደው የአዳዲስ አመራር ምርጫ ላይም በአሁኑ ጊዜ ፓርቲውን በፕሬዚዳንትነት እያገለገሉ የሚገኙት ኢንጂነር ይልቃል፣ ፓርቲውን ለቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት በመሪነት ለማገልገል በዕጩነት እንደሚቀርቡ አረጋግጠዋል፡፡
በሰማያዊ ፓርቲ መተዳደርያ ደንብ መሠረት አንድ አባል ፓርቲውን ለመምራት ሁለት ጊዜ እንዲወዳደር ይፈቅዳል፡፡ ኢንጂነር ይልቃልም በዚህ ደንብ መሠረት ዳግም ፓርቲውን ለማገልገል እንደሚወዳደሩ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ስለሚኖረው ውድድርና እነማን ተፎካካሪዎቻቸው ሊሆኑ እንደሚችሉ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹እስካሁን ድረስ በግልጽ ራሱን ለፕሬዚዳንትነት ዕጩ አድርጐ ያቀረበ ተወዳዳሪ አባል የለም፡፡ እኔ ግን ለምክር ቤቱም ሆነ ለሚመለከታቸው አካላት ለፕሬዚዳንትነት እንደምወዳደር ይፋ አድርጌያለሁ፡፡ ተወዳዳሪዎች እንደሚኖሩ ጥርጥር የለውም፡፡ እስካሁን ይፋ ያደረገ ግን የለም፤›› ብለዋል፡፡
በፓርቲው መተዳደርያ ደንብ ላይ ጠቅላላ ጉባዔ በየአንድ ዓመቱ እንደሚሰበሰብ ይደነግጋል፡፡ ይሁንና እስካሁን ድረስ ጠቅላላ ጉባዔ ተጠርቶ አያውቅም፡፡ ያልጠራችሁት ለምንድነው ለሚለው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹በየዓመቱ የሚለው እንደ ሁኔታው ነው የሚወሰነው፡፡ ፓርቲው በራሱ አስፈላጊ ነገሮች ሲኖሩና ጉባዔው ቢያያቸው ጥሩ ነው በሚል እሳቤ በየዓመቱ ጠቅላላ ጉባዔ ሊያካሂድ ይችላል እንጂ፣ በአስገዳጅነት በየዓመቱ መካሄድ አለበት የሚል ነገር የለም፡፡ በአስገዳጅነት መካሄድ አለበት የሚለው የሦስት ዓመቱ ነው፤›› ብለዋል፡፡ 
‹‹የጠቅላላ ጉባዔ ሥልጣን ትልቅ ነው ይባላል፡፡ ነገር ግን በተግባር ደረጃ ሲታይ ግን በሦስት ዓመት አንዴ ነው የሚሰበሰበው፡፡ ያንን ለምን አንቀይረውም በማለት በዚያ መሠረት ነው ደንባችን ውስጥ ያካተትነው እንጂ፣ የጠቅላላ ጉባዔው የሥልጣን ዘመን ለሦስት ዓመት ጊዜ ነው፤›› በማለት ጨምረው አስረድተዋል፡፡
የፓርቲው መተዳደርያ ደንብ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሥልጣንና ተግባር በሚመለከት የሚደነግገው አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ 13፣ ‹‹የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በድጋሚ ካልተመረጡ በስተቀር የሥራ ጊዜያቸው ሦስት ዓመት ይሆናል፡፡ በሊቀመንበርነት የኃላፊነት ቦታ ማገልገል የሚቻለው ለሁለት ተከታታይ ዙሮች ብቻ ነው፡፡ ሆኖም ከአንድ የሥራ ዘመን ዕረፍት በኋላ ተመልሶ ለዚያው ቦታ ሊመረጥ ይችላል፤›› ይላል፡፡ ይሁን እንጂ ጠቅላላ ጉባዔው መደበኛ ጉባዔውን በዓመት አንድ ጊዜ ማካሄድ እንዳለበት ደንቡ በአንቀጽ 24 ላይ ይደነግጋል፡፡ ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ቢያጋጥምም ማራዘም የሚቻለው ለሦስት ወራት ብቻ እንደሆነ ያሰፍራል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ያሉት አስገዳጅ የሆነ የጉባዔው ስብሰባ በየሦስት ዓመቱ እንደሆነ የሚገልጽ አንቀጽ ግን የለም፡፡ 
የፊታችን ቅዳሜና እሑድ በሚካሄደው የፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔ በአጠቃላይ የነበረውን የፓርቲውን ጉዞ እንደሚገመገም የተገለጸ ሲሆን፣ በተጨማሪም ፓርቲው አሁን ካለበት ተነስቶ ምን ማድረግ አለበት የሚሉትን ጉዳዮች፣ እንዲሁም አጠቃላይ የአገሪቱንና የቀጣናውን የፖለቲካ ሁኔታ በመዳሰስ አቋም እንደሚወሰድ ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል፡፡ 
በጠቅላላ ጉባዔው ለመሳተፍ ከመላው አገሪቱ የተውጣጡ 250 ያህል የፓርቲው አባላት እንደሚወከሉ ገልጸው፣ ‹‹ጠቅላላ ጉባዔውም ጠንካራ የትግል መንፈስ ለመፍጠርና ፓርቲው የነበሩትን ጠንካራና ደካማ ጐኖችን ገምግሞ፣ በጠንካራዎቹ ላይ የበለጠ ለመሥራት፣ ደካማ ጐኖችን ደግሞ እየቀረፈ በመሄድ ተጠናክሮ ለመሥራት አቅጣጫ ይቀመጣል፤›› በማለት ኢንጂነር ይልቃል የጠቅላላ ጉባዔው ውጤት ምን ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ በይፋ መመሥረቱን ያወጀው ታኅሳስ 2004 ዓ.ም. ላይ የነበረ ቢሆንም፣ በምሥረታው ወቅት ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባቱ የሚታወስ ነው፡፡ 
ፓርቲውንና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን አወዛግቦ የነበረው ጉዳይ ደግሞ ፓርቲው ያቀርበው የነበረ የሕግ አግባብ ነው፡፡ ይህም አንድ ፓርቲ የምሥረታ ጥያቄውን ለምርጫ ቦርድ ባቀረበ ሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ ምላሽ ካልተሰጠው ዕውቅና እንደተሰጠው ይቆጠራል የሚለው ነው፡፡ በዚህም መሠረት ፓርቲው በታኅሳስ 2004 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ መመሥረቱን ይፋ ሲያደርግ፣ ከምርጫ ቦርድ ዕውቅና አግኝቶ መንቀሳቀስ የጀመረው ግን ከሐምሌ 3 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ ነው፡፡
Source: Reporter

Sunday, August 16, 2015

"ግጥም እንደ አልጌ ሲፋቅ ጭረት አለው"

ሀያሲ አብደላ እዝራ:-
ዛሬ ቅዳሜ ነው! በዚህች ቀን በርካታ አስደሳች የህይወት አጋጣሚዎች አልፈዋል:: ካለፉት ጊዜያቶች ሁሉ ደግሞ የዛሬ ልዩ ነው፡፡ ለብዙ ዓመታት ደንበኛ በሆንኳትና በምወዳት አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ በስነፅሁፍ ህይወቴ ለራሴ ክብር የሰጠሁበትና ወደፊት ጠንክሬ እንድፅፍ ምርኩዝ የሆነኝ አስተያየት በአካልም ሆነ በመልክ የማላውቀው ሀገራችን በኪነጥበብ ዘርፍ ካፈራቻቸውና በስነ ፅሁፍና ግጥም ዙርያ ጠንካራ ሂስ በመስጠት የሚታወቁት ሀያሲ አብደላ እዝራ እጅ የግጥም መፅሀፌ ገብታ ከፍተኛ ትኩረት አግኝታ ተገምግማ ለወደፊት ስራዬ የሚያስፈነጥረኝን እርካብ እንደመርገጥ ምን የሚያስደስት ነገር አለ?!::
እኚሁ ሀያሲ ማክሰኞ ነሀሴ 12/2007 ዓም በፑሽኪን አዳራሽ ከምሽቱ 11 ጀምሮ በተሰናዳው የመፅሀፍየምረቃ ዝግጅት ላይም እንደዚህ ቀልባቸውን ስለሳበችው መፅሀፍ ከዚህ ለየት ያለ ሙያዊ አስተያየት ሊያቀርቡ ፕሮግራም ተይዞላቸዋል፡፡ እኔም እኚህን ሰው እኩል ከናንተ ጋር ለማየት ጓጉቻለሁ፡፡
የዛ ሰው ይበለን
መልካም ቅዳሜ