Tuesday, September 15, 2015

የወቅቱ ቀዳሚ አጀንዳ!!!!

የወቅቱ ቀዳሚ አጀንዳ!!!!
(ሱራፌል ሐቢብ)
ማን ነው የሚታመን?? ማን ነው የህቡዕ ስራ አና ሴራ ተባባሪ ያልሆነ??? ማን ነው አስመሳይ? የቱ ነው ትክክለኛና አውነተኛ??? ስንቶቻችንስ እንሆን የሞላ ቢጤዎች???!!! ማንስ ማንን አንዴት ማመን ይቻለዋል?!!!! የገዛ ጥላው የራሱ ስለመሆኑ ማን ነው አርግጠኛ??? አርሱ ማን ነው? አርሷ ማን ናት? አንተ ማን ነህ? አነቺ ማን ነሽ? አነርሱስ አነማን ናቸው? አኛስ ከወዴት ነን??? ከሁሉ በላይ እኔ ማን ነኝ??? አነዚህ ሁሉ በዚህ ስርዓት ላይ አንደየአቅማችንና አውቀታችን ትችት የምንሰነዝር ሁሉ አራሳችንን ልንጠይቀው የሚገባ ወቅታዊ እና አንገብጋቢ ጥያቄዎች ናቸው!!!
አርስ በርስ በዓይነቁራኛ አየተያየን፣ አንዱ ሌላውን እየሰጋ አንዲኖርና፤ መተማመን በሌለበት ጉዞ ስንዳክር እንድንከርም በመኸል ሰርገው በሚገቡ ጥቂት ሆዳሞች ተስፋ ልንቆርጥም የሚገባ አይደለም!!!!!!
የዘመኑን የኢትዮጵያ የሰላማዊ ትግል ፖለቲካ ከማንም በላይ ያዳከሙትና ለሁልጊዜውም ባለበት አንዲረግጥ የዳረጉት “ሆዴን ከሞላሁ ምኔን ጅብ ይብላው” አንዳለችው አህያ ህሊናቸው ከከርሳቸው ባነሰባቸው ቀሽም ሰርጎ ገብ ካድሬዎች ለመሆኑ ለማንም ግለፅ ነው፡፡
በዚህ ወቅት በሰላማዊ ትግሉ የፖለቲካ አንቅስቀሴም የሚንቀሳቀስ ሁሉ አስቀድሞ ከእነዚህ አስመሳይና ስውር ሴረኞች አራሱን መከላከል፣ ማፅዳት አና መጠበቅ ይኖርበታል!!
አሁንም በአንፃራዊነት የተሻለ አንቅሰቃሴ አና ጥንካሬ አላችሁ ብዬ የማስበው መደረክ እና ሰማያዊ ፓርቲ ይህን የሰርጎ ገቦችን ሴራ በየድርጅታችው የማጥራት ስራ ካልሰራችው እና ለተግባረዊነቱ ካልፈጠናችው የቀድሞው ቅንጅት፣ የአንድነት እና የመኢአድ እጣ ተካፋይ ከመሆን አንደማትድኑ ምንም ጥርጥር የለውም!!!!!
ማንም ስለማንም ማንነት የማይጨነቅበት፣ መተማመን የሰፈነበት የፖለቲካ አንቅስቃሴ መፍጠር የትክክለኛው ጠቃዋሚ ፓርቲ ቀዳሚ አጀንዳና መለያ ይሁን!!! እባቡ ከእርግቡ፣ ፍሬው ከገለባው ፣ ስንዴውም ከአንክርዳዱ ይለይ!!!!!!!!!!!!!!!!

0 comments