Wednesday, October 14, 2015

ነፃነት! ነፃነት! ነፃነት!



ነፃነት! ነፃነት! ነፃነት!
(ሱራፌል ሐቢብ)
    ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አሳቡን በነፃነት የመግለፅ እና የመፃፍ መብቱን በአግባቡ ስለተጠቀመና የፍርሀት መንፈስን ድል ነስቶ በሀገሬ ጉዳይ አኔም ያገባኛል በሚል እሳቤ እውነትን በመያዝ የሐሰተኞችን የጉድ ከረጢት በብዕሩ ሸንቁጦ ነውራቸውን ለአደባባይ ስላበቃ ወህኒ ከተጣለ እነሆ ዛሬ (ጥቅምት 3/2008 ዓ.ም) ድፍን አንድ አመት ሞላው፤ የአምባገነኖች ስርዓት በተፈጥሮአዊ ባህሪው ብረት አንስቶ ከሚፋለመው ኃይል ይልቅ ብዕር ጨብጦ የሚሞግተውን አንድ ግለሰብ እጅግ ይፈራል ፤ይህ አንዱ የአምባገነኖች መለያ ባህሪ ነው! ምክንያቱም ብረት ያነሳውን ኃይል በብረቱ መመከት ይቻለው ይሆናል ነገር ግን የብዕረኞችን አሳብ በተሻለ አሳብ የሚሞግትበት እና የሚመክትበት አቅምና ችሎታ ስለማይኖረው ያለው አማራጭ እነርሱን ማሰር፣ ከሀገር እንዲሰደዱ ማድረግ ግፋም ካለ ማስወገድ ነው፡፡ መፃፍ ወንጀል፣ መናገር ሐጢያት፣ አሳብን በነፃነት መግለፅ' ነውር የሚሆነው ከማንአለብኝነት ከሚመነጭ የአምባገነኖች ስርዓት ውጪ ሌላ በምን ሊሆን ይችላል?

0 comments