ሀበሻነቴን
ያለቅጥ
እወደዋለሁ፡፡ኢትዮጵያዊነቴን
የምወደው
ማንነቴ
ብቻ
ሳይሆን
መደነቂያዬ፣የአግራሞቴ
ምንጭ፣የመደነቅ
ጥበብ
ያወረሰኝ
ስጦታዬ
ስለሆነም
ጭምር
ነው፡፡ሀበሻና
ሀበሻዊነት
ለእንደኔ
አይነቱ
ለአድናቂና
ተደናቂ
የእውቀት፣የጥበብ፣የትዝብት፣የፌዝና
የሳቅ
መፍለቂያ
ከመሆን
በላይ
ሰርክ
በአድናቆት
የሚወዘውዝ
ሀበሻዊ
መልክ፣ኢትዮጵያዊ
ገፅ
እና
ቀለም
ጋር
ባንድነት
ከሌላው
ዓለም
ሰዎች
በተለየ
ሁናቴ
በኢትዮጵያዊ
ማንነትና
ሰውነት
ተውቦና
ተኩሎ
የሚገኝባት
በዚህችው
እኔኑ
መሽቶ
በነጋ
ቁጥር
በምታስደምመኝ...
ለድማሜ
በተፈጠርኩባት፣በፈጠረችኝ
ሀገር
እና
ወገን
መሀል
ስላለሁ ይመስለኛል፡፡
የሀገሬ
ሰው
ብዙ
ነገሩ
ድንቅ
ይለኛል...አንዳንዴ እግዜሩ እኔን ብቻ ነው እንዴ በትንሽ-በትልቁ፣በረባው
ባልረባው
አስገራሚ
ሳይሆን
ተገራሚ
አድርጎ
የፈጠረኝ
እያልኩ
እገረማለሁ...ሁሌም ዓውደ-ዓመት በመጣ ቁጥር አግራሞቴን የሚጭረው ጉዳይ አንጀት የሚበላው ሀበሻዊ አንጀታችን ነው፡፡ሀበሻና አንጀት ያላቸው ትውፊታዊ፣ስነልቦናዊ ቁርኝት ከመደነቂያ
ሀበሻዊ
ጉዳዮቼ
አንደኛው
ነው፡፡
መደነቄ
ቅጥ
እና
ወደር
የለውም
የምላችሁ
ከልቤ
ስለሚያስደንቀኝ
ነው፡፡ለምን
ቢሉ
በምድራችን
ላይ
አንጀት
የሚበላ፤አንጀቱም
የሚበላ
ህዝብ
ኢትዮጵያዊ
ብቻ
ይመስለኛል፡፡እንዴት?!...ለምን ካላችሁ?!...ይኸው አስረጂ
በላሽው አንጀቴን በላሽው
በላሽው አንጀቴን በላሽው
ሸገር አዲሳባ ሸዋ ላይ ያለሽው
እያለ
በዘፈንና፣በግጥም
አንጀት
የሚበላና፣አንጀቱ
የሚበላ
ህዝብ
በሌላው
ዓለም
ስለመኖሩ
እጠራጠራለሁ፡፡ለአንጀት
ልዩ
ፍቅር
አለው
ህዝቤ፣...ለአንጀት ልዩ ስፍራ አለው ያገሬ ሰው፣...አንጀት ቅኔው፣አንጀት
ሰምና
ወርቁ
ነው
ወገኔ...አንጀት መለያው፣አንጀቱ
መታወቂያው
ነው
ሀበሻ...ባንጀት እና ባንጀቱ ፌዝ አያውቅም...ሀበሻን ባንጀትና በሆዱ አትምጡበት...ከመጣችሁበት
ግን...
አንጀቴና ሆዴ ተጣልተውብኝ
አንተም ተው ፣አንተም ተው እንዳልላቸው
አንጀቴም አንጀቴ፤ሆዴም-ሆዴ ነው
ይላችኋል፡፡
ሀበሻ
አንጀት
ሲበላ
አልቦ
ነው
የሚበላ...አንጀት ገምዶ፣ፈትሎ
ነው
የሚበላ...አንጀት አድቅቆ ነው የሚበላ...የሚበላው የሰው አንጀት ቢያጣ የከብት አንጀት በፍቅር ይበላል ያገሬ ሰው፡፡በልዩ
ሀበሻዊ
ጥበብ
እና
ብልሃቱ
በቅመም
አሳብዶ
በቃሪያ፣በጥብስ
ቅጠል፣በነጭ
ሽንኩርት
አቁላልቶ፣ዶልቶ...ዱለት አርጎ...አንጀት ጠብሶ፣አንጀት
ለብለብ
አርጎ
አሊያም
በጥሬው
አንጀት
ይበላል
ኢትዮጵያዊ፡፡
ያገሬ
ሰው
አንጀት
መብላት
ያውቅበታል፡፡ሀበሻ
በግ
የሚያርደው
ለዱለት
ካለው
ጥልቅ
ፍቅር
የተነሳ
ይመስለኛል፡፡አንጀት
ለመብላት
ይመስለኛል፡፡ሀበሻ
ዱለት
ማልዶ
ሳይቀምስ
ቅልጥም
አይቀለጥምም፣ፍሪምባና
ጎድን፣ሳላይሰጥና
ወርች
አያምረውም፡፡ዱለት
ዓውደ-ዓመት ማድመቀዊያው
ነው፤...ሀበሻ በዓል-በዓል የሚሸተው የትኩስ ዱለት መዓዛ አፍንጫውን
ሲኮረኩረው፣ሰርኑን
ሰርስሮ
ሲገባ
ነው፡፡የዱለት
መዓዛ
ከጠጅ-ሳር፣አሪቲ፣ጤናዳም፣ከከርቤና
እጣን
ጢስ፣ከጠጅና
ጠላው፣ከቁሌት
ጋር
የተደባልቆ አየሩን ሲሞላው...ይኼን ዱለታዊ የማለዳ አየር ማግ-ማግ ሲያደርግ ነው ዓውዳመቱ ዓውዳመት የሚመ ስለው...በዓሉ በዓል የሚሆንለት፡፡
ለሀበሻ
ዱለት
የሌለበት
በዓል
ትዝታ
የለውም፣ጎደሎ
ነው፡፡...አንጀት የሚያቃጥል፣አንጀት
የሚለበልብ፣አንጀት
የሚያነድ
ዓውዳመታዊ
ጠባሳ
ጥሎበት
ያልፋል፡፡ሀበሻ
በዓል፣ድግስ፣ሰርግና
ተዝካር
የማይለየው
አንጀት
ለመብላት
ይመስለኛል፡፡ለዚህ
ነው
ኢትዮጲያውነቴ
አንጀቴን
የሚበላው፣አንጀቴን
የሚያንሰፈስፈው፡፡
ሀበሻ
ክፉ
ቀኑን
የሚችለው፣መከራና
ስቃዩን፣በደል
እና
ጭቆናውን፣የመገፋት
ቁጭቱን
የሚያዳፍነው
አንጀቱ
ስር
ነው፣ካንጀቱ
ቀብሮ
ነው፤
ባገሬ
ሁሉን
ቻይ
አንጀት
ያለው
ሰው
ይቀናበታል፡፡ያገሬ
ሰው
ሲኩራራ
የዝሆን
አንጀት
ሰጥቶኛል
ይላል፤ክፉና
በጎውን
እንዳመጣጡ
የሚቀበልበት
ሰፊ
ሆድ
እና
ባለገበር
አንጀት
የሰጠውን
ፈጣሪውን
ተመስገን
ብሎ
የባሰ
አታምጣ
እያለ
የሚኖረው
ባንጀቱ
ድንዳኔ
እና
ክሳት
ልክ
ነው
ብሎ
ያምናል፡፡ላበሻ
ረጅሙ
አንጀቱ
የኑሮ
ማሳለጫው፣ከክፉ
ቀን
መሰወሪያው
፣መሸሸጊያው
ነው፡፡
ወገኔ
የነገር
መክተቻ
ስልቻው፣እውነተኛ
ስሜቱን
መደበቂያ
ጎተራው፣ክፉና
ደጉን
ማጎሪያ
ጉረኖው
አንጀቱ
ነው፡፡ያገሬ
ሰው
የልቡን-በልቡ ያንጀቱንም-ባንጀቱ መያዝ የተካነ ዚቀኛ ነው፡፡እንኳን
ለባዳ
ለወዳጁም
ያንጀቱን
አያወጣም፣መዋደድ
እንዳለ
መጣላት
ይመጣል
ብሎ
አርቆ
አስቦ
አንጀቱን
ያርቃል፡፡ሀበሻ
ሀዘን
ደጁን
ረግጦ፣ከቤቱ
አልወጣ
ቢለው...ልብና አንጀቱን ጠብስቆ ሲያብሰከስከው
አንጀቴ
ተላወሰ፣አንጀቴ
ተንሰፈሰፈ፣አንጀቴን
በላኝ
ይላል
የሀዘኑን
ጥግ
ሊገልፅ
ሲፈልግ፡፡
ሀበሻ
ያመነው
ሲከዳው፣ወዳጄ
ያለው
ፊቱን
ሲያዞርበት፣የኔ
የሚለው
ሰው
ቃሉን
በልቶ፣እምነቱን
አጉድሎ
፣ማተቡን
በጥሶ
ዋሾና
ቀጣፊ
ሆኖ
ሲያገኘው
አንጀቴ
ተቆረጠ፣አንጀቴ
ተበጠሰ
ብሎ
ቅያሜውን
የሚገልፀው
አንጀቱን
ምሳሌ
አርጎ
አንጀቱን
ተውሶ
ነው፡፡
የሀበሻ
ሰው
ፍቅሩ
እንጂ
መቼም
ጠቡ
አያድርስ
ነው፡፡ሀበሻ
መውደዱ
እንጂ
ጥላቻው
ለጉድ
ነው፡፡ሀበሻ
ያቄመ
እንደሁ
አይጣል
ነው፡፡ሀበሻ
እንኳን
ቂም
እና
ጥላቻውን
ፍቅሩን
መሰወሪያ
ስልቻው
አንጀቱ
ነው፡፡ሀበሻ
አንጀቱ
ዋሻው
ነው፡፡አንጀቱ
ራስ
መደበቂያው
አመሉን
መክተቻ
አቁማዳው
ነው፡፡ሀበሻ
ነገር
ማሰንበቻ፣ማኮምጠጪያ፣ማርጊያ
አካሌ
አንጀቴ
ነው
ይላል...ነገር ሲገባው ተው ቻለው አንጀቴን ማንጎራጎር
ልማድ
አለው፡፡ሀበሻ
ፍቅርና
ደግነቱን፣የክፋትና
ጥላቻ
አብሲቱን
የሚጥለው፣የሚያብላላው፣የሚደፈድፈው፣የሚያፈላው
፣የሚያቀዘቅዘው
ባንጀቱ
ውስጥ
ነው፡፡
ሀበሻ
እንኳን
ለወዳጁ
ለራሱም
ስውር
ነው፡፡ወሬና
ነገር
ከሆዱ
ማይረጋለት፣ካንጀቱ
ማይቀመጥለት
ሀበሻ
ነውረኛ
፣ምስጢር
መቋጠሪያ
የሌለው
ወሽካታ፣ወናፍ፣አንድ
አይውል፣
ቁምነገረ-ቢስ፣ ከንቱ ተደርጎ ይብጠለጠላል፡፡ሀበሻ
አንጀተ
ደንዳና
እንጂ
አንጀተ
ወንዋና፣አንጀተ
ከሲታ
ጥሎበት
አይወድም፡፡አንጀተ
ልፍስፍስ
ሰው
ጀግና፣ደፋር፣ጎበዝ፣ብርቱ
ከሚውልበት
አደባባይ
አይውልም፤
ካንድ
ማዕድ
አይቆርስም፡፡
ሀበሻ ደስ ሲለው፣የልቡ ሲደርስ፣ያሰበው ሲሳካለት፣የተመኘው
ሲሆንለት፣ስለቱ
ሲሰምርለት
አንጀቴ
ቂቤ
ጠጣ፣አንጀቴ
ራሰ
ብሎ
የደስታ
ጥሙን
የሚቆርጠው፣የእርካታ
ፅዋውን
የሚጨልጠው
ወደ
አንጀቱ
ነው፡፡
ታዲያስ
እኔስ
ሀበሻ
አይደለሁ
አንጀት
መብላት
የለመደ
ሀበሻዊ
አንጀቴ
አውደ-ዓመት ሲመጣ ናድ-ናድ ፣ፍርስ-ፍርስ ይልብኛል...የዘንድሮው
በአል ደግሞ ባዲስ ህዳሴያዊ ፍቅር አንጀቴን ያንሰፈስፈው ይዟል!...ተሳለጥ-ተሳለጥ ይለኛል…ጂቲፒ-ጂቲፒ ይለኛል…ተናገር-ተናገር ይለኛል…ቃሊቲ-ቃሊቲ ይለኛል…ጉባዔ-ጉባዔ ይለኛል….እንብላ-እንብላ ይለኛል…እሰር-እሰር ይለኛል…አሸባሪ-አሸባሪ እያለ ሽብር ይለቅብኛል…ፍትህ-ፍትህ ይለኛል…ተሰደድ-ተሰደድ ይለኛል…ሀገር የለህም ይለኛል…አንጀቴ ስሩ ይመረኛል…እልህ አንጀቴን ያስልበኛል…ያልሄድንበት መንገድ ይቇጨኛል…የምናወራውና
ተግባራችን
ፍየል
ወዲህ
ቅዝምዝም
ወዲያ
ይሆንብኛል…አረ አይነጋም ወይ ያስቀነቅነኛል…የጨለማ ጉዟችን ማብቂያ አልታይህ ይለኛል…በመርከባችን
ካፒቴኖች
እንደ
ውሃ
ላይ
ኩበት
መዋለል
ታክቶኛል…አርበኝነት
እየከሰመ
ሞላጫነት
እየነገሰ
ሲመጣ
እያየሁ
የተስፋ
አንጀት
ርቆኛል…የሚያዋጣኝ
ይሄን
እሳትራታዊ
ሃሳብ
ወዲያ
ትቶ
አረ-ምኑን ሰጠሽ እያልኩ መዝፈን…አሊያም በዚህ አዲስ ዓመት ከቀናኝ አንድ ምኑ የተሰጣትን
ባለመቀመጫ
ፈልጌ
ከጢዟ
ስር
ተደብቄ
ይሄን
ክፉ
ቀን
ማሳለፍ…
ለናንተ
ለወገኖቼ
አውደ-ዓመት ሲመጣ የዱለት አምሮት የጠናበት፤
ሀበሻዊ
ሆድና
አንጀታችሁ
ለሚባባ
ከሀገር
እና
ቤተሰብ
ርቃቸሁ፣የስደት
ኑሮ፣የባዕድ
ሀገር
ህይወት
አልሞላ
ላላችሁ
መለየትና
ናፍቆት
አንጀታችሁን
ለሚበላችሁ፣...እናት እና አባታችሁን፣ባልና
ሚስታችሁን፣ወንድምና
እህታችሁን፣ፍቅረኛና
ልጃችሁን
ሞት
ቀምቶ
ሀዘን
አንጀታችሁን
ለሚያኝከው፣...በዘመኑ ፖለቲካ ያለወንጀላችሁ
ከእስርቤት
ተወርውራችሁ፣ዘብጢያ
ወርዳችሁ
በክፋት
ጓጉንቸር
ለተከረቸማችሁ፣በሆስፒታል
አልጋ
ላይ
በህመምና በስቃይ ላላችሁ፣ የምትወዷት ወይም የምትወዱት ልጅ ቤተሰብ ጥየቃ ሄዶባችሁ በመለየትና በብቸኝነት አንጀታችሁ ለሚላወስ እና ዱለት አልበላ ላላችሁ፣ለከፋችሁም-ደስ ላላችሁም፣ለሞላላችሁም-ለጎደለባችሁም...ለትንሾቹም
ለትልቆቹም...ለእናንተ ለወገኖቼ ለሁላችሁ አንጀት ሚወደው፣ዱለት
ያማረው
ሀበሻዊ
አንጀቴ
እስኪላወስ
እወዳችኋለው...መልካም አዲስ-ዓመት ይሁንላችሁ፡፡
0 comments