ትናንትና
“ቀይ
ሽብር”
ዛሬ
“የእስር
ሽብር”
ነገ
ደግሞ
…..........!!!
(ሱራፌል ሐቢብ )
ትናንት ታላላቅ ወንድም እና አባቶቻችን በጩኸትና በሰላማዊ ትግል ያሳኩትን አብዮት ጥቂት ጉልበተኛና አምባገነን ወቶአደሮች በማን አለብኝነት ሰርቀውና ከመንበረ ስልጣኑ ተፈናጠው አብዮቱን ንጉሳዊ እና ፊውዳላዊ ስርዓቱን ከማስወግድ ውጪ ትርጉም የለሽ አንዲሆን አስችለውታል፡፡ “ያለምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም” በሚል መርህ መላ ሀገሪቱን ከዳር አስከ ዳር “ቀይ ሽብር” በተባለ የጅምላ ግድያ አና ስቃይ ደም በደም አደረጓት፤ ብዙዎች ተገደሉ፣ታሰሩ፣ ተገረፉ እንዲሁም ተሰደዱ ይህ ሁሉ የደረሰባቸው ግን ነብሰ በላውን ስርዓት ስለተቃውሙ ብቻ ነበር፤ ከዚህ የተረፉ እና አማራጩ ትጥቅ ትግል ነው ብለው ያመኑ ዱር ቤቴ ብለው ነፍጥ ጨበጡ፤ ከእነዚህ ነፃ አውጪዎች መኸል የዛሬዎቹ የሚኒሊክ ቤተመንግሰት ሹማምንቶች በለስ ቀናቸውና የኢትጵያን ሕዝብ የዲሞክራሲ፣የብሔር እኩልነት፣የሰብዓዊ መብት እና ሌሎች ጥያቄዎች መልስ ሊሰጡ ተራቸው ደረሰ፤ እነሆም ዛሬ ላይ 24 ዓመታት ተቆጠሩ፡፡
አሁን ላይ ብዘዎች በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ሰለማይስማሙ፣ ፖሊሲዎችን ስለሚነቅፉ፣ ስለሀገር አንድነት፤ ስለሀይማኖት ነፃነት ስለታገሉ፣ የዘር ፖለቲካን ስለሚተቹ፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብታቸውን ተጠቅመው ስለፃፉ፣ ለፕሬስ ነፃነት ስለተቆረቆሩ፤ ይታሰራሉ፣ ይሰደዳሉ ሽብርተኛ የሚል ተቀፅላ ስም ይቸራሉ!! እናም ከብሶት የተወለደው፣ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ የብዘዉዎችን የነብስ እና የአካል መጉደል መስዋትነት ካስከፈለ ትግል የተገኘ ስርዓት እንዴት ይህን ለማድረግ ድፍረቱን አገኘ? አንዴትስ ከብሶት የተገኘው ስርዓት ብሶት ፈጣሪ ለመሆን ተቻለው?
ዛሬ ዲሞክራሲ ለመነገር ቀሎ ለተግባር የሚቸገረው፣ነፃ ፐሬስ በነፃነት እንዳያብብ በእሾህ የሚታጠረው፣ ጋዜጠኛና ጦማሪያን አንዲሁም ተቀዋሚ ፖለቲከኞች በሽብር ስም የሚታሰሩት ለነፃነት ታግያለሁ ለዲሞክራሲ ብዘዎችን በመስዋትነት ገብሬአለሁ በሚል ስርዓት ነው!! ነገስ????? ነገ ደግሞ ማንን ባለተረኛ አንደሚያደርግ አናውቅም!! በዚህ ሁሉ መኸል ግን የመሪ ፖለቲከኞቹ እዳ አወራራጅ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ሆኖ ነው እየቀጠለ ያለው፡፡ ትውልድ ያልፋል፣ ትወልድ ይተካል፤ ያም ይሔዳል፣ ይሄም ይመጣል ፤ የሚበጀን ግን እውነትንና አውነተኝነትን ይዞልን የሚመጣ ብቻ ነው፡፡

0 comments