Wednesday, September 16, 2015

"የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ"

"የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ"
(ሱራፌል ሐቢብ)

በተለመዱ ጠባብነት፣ ትምክህተኝነት፣ ኪራይ ሰብሳቢነት……እንትንነት………እገሌነት……… በተሰኙ ዲስኩሮች ላይ ባለፈው ጠቅላላ ጉባዬው ጉንጭ አልፋ ውይይት ሲያደርግ የከረመው ገዢው ፓርቲ ለቀጣይ
ጉባዬው አዋሳን መምረጡን ስሰማ እንደው ልፋ ያለው ስብስብ መሆኑ አስገረመኝ! ለምን ቢባል በቀጣይ አምስት ዓመታት ለጠቅላላ ጉባኤ ከተማ ለከተማ መዃተን ሳይጠበቅበት ፓርላማውን እንደጠቅላላ ጉባኤ መጠቀም መቻሉን እኛ አስክንነግረው ድረስ መጠበቅ አልነበረበትም! የሰሞኑ ጠቅላላ ጉባኤ ከመጪው ፓርላማ በምን ይለያል? በምንም!! “የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታይሉዋል ይሔ ነው!! በጠቅላላ ጉባኤው አጋሮች ነበሩ፤ በቀጣዩ ፓርላማም አጋሮች ብቻ ከገዢው ጋር አሉ፤ በጠቅላላ ጉባኤው ወዳጆች አና ታዛቢያን የተባሉ ተሳታፊዎች እንደነበሩ ሰምተናል፤ በአዲሱ ፓርላማም አንዳለፉት የፓርላማ ዘመናት ከላይኛው የእንግዶችና የታዛቢያን ሰፍራ አኒህ ወዳጅና ትዝብተኞች እንደሚኖሩ ይጠበቃል!! በጠቅላላ ጉባኤያቸው ሁሉም በአንድ አሳብ አንደተስማሙት፤ በፓርላማው ውስጥም በማንኛውም ነገር ላይ ሁሉም አንደጉባያቸው በአንድ አንደሚስማሙ ጥርጥር የለውም፡፡ ለእኔ ቀጣዩ ፓርላማ እና የገዢው ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው!!!!



0 comments