“ተይ ሀገራችን”
በዘመናችን ሐሰት ከአጥንትና ደም ተሰርቶ
፣በሰው አምሳል ስጋ ለብሶ በተሸከርካሪ
ወንበር ተቀምጦ አየተንፈላሰሰሰ
ከፊቱ ደምፅ ማጉያዎችን ፣ በቀኝና
በግራው ቅጥፈቱን የሚነዙለትና የሚያራግቡለት ጋዜጠኛ ተብዬዎች ደርድሮ ውሸቱን ሲለቀው ያልተመለከተ ኢትዮጵያዊ ለመኖሩ እጠራጠራለው፤ በግምት ከወርና አስራ አምስት ቀን በፊት
ይመስለኛል በሐገራችን ሰሜን ምስራቅ ፣ በስምጥ ሸለቆና የምስራቁ ክፍል ስለተከሰተው
ድርቅ ይህ ስጋ ለባሽ ሐሰት የድርቁ ሁናቴ የማያሰጋ ፣ መንግስትም ይህን አደጋ መቆጣጠርና መመከት አንደሚችል
በድፍረት ተናገረ አንደውም እንኳን ሰው ሊሞት ቀርቶ አንስሶቹም የሞቱት በእረኞች ቅሽምና አንጂ በድርቁ ሳቢያ አንዳልሆነ አክሎ ደሰኮረ መች ይሔ ብቻ የማንንም አርዳታና ድጋፍ አንደማይሻ አበክሮ ከገለፀ
በኃላም በራስ አቅም ችግርን የመቋቋም እና የመፍታት ደረጃ ላይ የደረሰች ሐገር ዛሬ ላይ መፈጠሯን፣እራሷን በሙሉ አቅም መመገብ
የቻለች ኢትዮጵያ መገንባቷንም አስረግጦ ሳያፍር እና ሳይፈራ በማን አለብኝነት ደሰኮረ፡፡
ይህ በሰው አምሳል የተገለጠ
ሐሰት ይህን ብሎ ባለ የሳምንት ጊዜ ውስጥ አለቃው በአንድ ትልቅ አዳራሽ ውስጥ “ራሳችንን በምግብ ችለናል፣ አንኳን
እኛ ካሊፎርኒያና አውስትራሊያም በድርቅ እየተሰቃዩ ነው፣ ከዚህ በፊት ድርቅ ሲከሰት ሮጠን ወደ ውጪ ድጋፍና አርዳታ ልመና ነበር የምንሔደው አሁን ግን ያ! ታሪክ ሆኗል………………….ምናምን ምናምን” አሉና ተጨበጨበላቸው!!! ግና ያጨበጨቡ እጆች ግለት ሳይበርድ፣ የዲስኩሩና
የጩኸቱ ድምፅ ርግብግቢት ሳይጎድል በዚህ በተገባደደው ሳምንት ይህ ሐሰተኛ አምሳለ ሰብእ በወትሮው ወንበሩ ላይ ፊጥ አለና ከፊቱ
ለተደረደሩ ጋዜጠኞች ልማዱን ሊያደርስ ተደነቀረ፤ ከወር በፊት ስለተናገረው ረስቶ ይሆን (ውሸት'ኮ ይረሳል) ወይም በተለመደ ማን አለብኝነት ተደፋፍሮ ይሁን ብቻ አኔ አልገባኝም!
፡ ስለድርቁ ሁኔታ ሲናገር የተጎጂዎች ቁጥር በእጥፍ አንደጨመረና፣ የተጎዱ ዜጎችን ለማቋቋም ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተጠበቀው ድጋፍ አንዳልተገኘ መሰከረ፣
የውጪ ድጋፍና አርዳታ አንደሚያስፈልግ በመንግሰትና በረጂዎች ታምኖበት ወደ እንቅስቃሴ አንደተገባም ቃሉን ሰጠ፡፡
ታዲያ
አስቀድሞ ጉራን መንዛት ለምን አስፈለገ? አውነቱን ለሚያውቀው የኢትዮጵያ ህዘብ ይህ ንቀት ነው!!! “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ” የሚል
ብሒል ላለው ማህበረሰብ ይሔ ስድብ ነው!!! ያልተፈጠረ አቅም አንደተፈጠረ በፈጠራ ወሬ ማሳመን ሊያውም ሕዝብን አንዲህ ቀላል'ኮ
አይደለም፤ የእለት ተለት ኑሮው ምን እንደሚመስል ከህዝቡ በላይ እነእንትና ሊያውቁት አይችሉም፤ መሬት ላይ ያለው ሌላ ነውና፤ አነርሱ
ካሉበት የከፍታ ቦታም ሊነፃፀር አይችልም ምክንያቱም መሬት ላይ አውነት
በሽ ነው ከከፍታው ስፍራ ግን ሐሰት ነግሷል!
የንጉሳዊው
ስርዓት ማክተሚያ የነበሩት ንጉስ በጊዜው የተከሰተውን ድርቅና ረሀብ ሸሽገው ለውሻቸው ልደት የ5ሺህ ፓውንድ ኬክ በመቁረስ፣ ከመኳንንትና
መሳፍንቶቻቸው ጋር ውሰኪ በመራጨት ትልቁን ታሪካዊ ስህተት ፈፀሙ፤ እርሳቸውን ተከትለው ሀገሪቱን
ለመመምራት አራት ኪሎ ቤተመንግሰት የገቡት ወታደሮችም ሕዝቡን ከረሐብና የድርቅ ሰቆቃ ሊታዱጉት አልተቻላቸውም፤ የዛሬዎቹ ደግሞ
ጆሮአችን አስኪደማ በውሸት ያደነቁሩናል፣ በዓይናችን የምናየውን ሐቅ ገልብጠው ይነግሩናል፣ የሌለ ነገር አለ ይሉናል!!! አሁንስ
ያ ጎበዝ ድምፃዊ አንዳዜመው “ተይ ሀገራችን” ማለት አሰኘኝ!!!
“ተይ ሀገራችን፤ ተይ ሀገራችን
እናኔ፤ እናኔ፤ እናኔ፤
እናኖ፤ እናኖ፤ እናኖ”
0 comments